ለዘብተኝነት: የከሸፈ የፖለቲካ አቅም

በአገሪቱ የአጭር ጊዜ የዴሞክራሲ ተሞክሮ ውስጥ ብልጭ ብሎ የጠፋ የሚመስል የፖለቲካ ትግል አካሄድ ነበር። በትግል አካሄዱ መሀል ሰፋሪ የሚባለው የፖለቲካ አካሄድ ከሁለት  ጫፎች መካከል የሚገኝ ሚዛናዊ የሆነ የፖለቲካ አካሄድ ነው።


በ1997ቱ ምርጫ መጨረሻ አካባቢ ራሱን የገለጠው ይህ የፖለቲካ አካሄድ አቋሙ የመንጋ ግርግር የፀዳ ፣ ከመንግስት ተፅእኖ የተላቀቀ ውሳኔውን በራሱ የትግል መርህ መሰረት የሚተገብር ነበር። በግሌ ባለኝ ግንዛቤ ይህ ለዘብተኛ የፖለቲካ አካሄድ በአቶ ልደቱ አማካኝነት ወደ ፖለቲካዊ መድረኩ እንደመጣ መገመት ይቻላል።

የበፊቱ የፖለቲካ ወለምታ

ከምርጫ 97 በፊት የአገሪቱ ፖለቲካ በሁለት ፅንፍ የሚንቀሳቀሱ አክራሪ ፖለቲከኞች እሰጣ ገባ የተሞላ ነበር። አብዛኛውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ የተቆጣጠረው ኢህአዴግ በራሱ የፖለቲካ አላማ ላይ " ትግል - እስከመቃብር" የሚል ፅንፍ የያዘ አቋም ነበረው። ይህ አቋሙ ሁለት ነገሮችን አስከትሏል። የመጀመሪያው ድርጅቱ ውጪው ያለውን የፖለቲካ ፍላጎት ለመረዳት አቅም እየሸረሸረው ሄዶ በ 97ቱ ምርጫሄዶ በተቀጥቶ እንዲገነዘብ አድርጎታል። ሁለተኛው ተፅእኖ ከኢህአዴግ በተቃራኒ ፅንፈኛ ፖለቲከኞችን እንደ አሸን ፈልፍሏል። በሁለቱ ፅንፍ የፖለቲካ ኃይሎች የስንግ ተይዞ የቆየው ፖለቲካ ለዛውን አጥቶ ሞት ሞት የሚሸትበት፣ ብስለት የጎደለው ሙሉ በሙሉ የስሜት ፖለቲካዊ አካሄድን ፈጥሯል። ለዘብተኛው የፖለቲካ ትግል በሁለቱ ልንፍ መካከል ብልጭ ብሎ ከታዬ በኋላ እንደገና የፅንፈኞቹ ሰለባ ሆኖ ጠፍቷል።

image

የከሸፈው አቅም

ለዘብተኛ የፖለቲካ ትግል ከፅንፈኞቹ የሚሻልበት በርካታ ፖለቲካዊ አቅሞችን መጥቀሰስ ይቻላል። የመጀመሪያው አጀንዳ የህዝብ  ማድረጉ ነው። ሁለቱ ፅንፈኞች የፖለቲካ አጀንዳውን ከራሳቸው ጥቅም አንፃር የሚቃኙ ነበሩ። ለምሳሌ የኢህአዴግ ፅንፈኝነት የግል ፖለቲካዊ ትርፍ ሲሆን የቅንጅት ፅንፍ የፖለቲካ አቋም ያልተገራ የመንጋ ተሳትፎ ነበር። በመሀል የወጣው ለዘበተኛው አካል ከሁለቱም ተገቢ የሆኑ ነገሮችን በመውሰድ አጀንዳውን ወደ ህዝቡ ለማስረፅ ሞክሮ ነበር። በሁለተኛ ደረጃ ለዘብተኛው የፖለቲካ ኃይልላ ከግላዊና ያልተገራ የመንጋ ግርግር ይልቅ እንቅስቃሴውን የዴሞክራሲ መርህ ላይ መሰረት ለማድረግ ጥረት አድርጎ ነበር። ከምንም በላይ በዚህ የለዘብተኛ የፖለቲካ የነበረውና የከሸፈው የፖለቲካ አቅም የጠላትነት ክፍፍል የሚያስቀር የአገራዊ ውህደትየአ አቅም ነበር። የፖለቲካ ኃይሉ ውግንና ከአጀንዳ አንፃር እንጂ ከተሳትፎ አንፃር የሚወሰድ ባለመሆኑ ለአገራዊ መግባባት ትልቅ ፋይዳ የነበረው ቢሆንም ቦታ ሳያገኝ የከሸፈ አቅም  ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

Comments

  1. I don't agree with this analysis for two reason. In the first place, Ato Ledetu's view was not something create to bring a third option into the political system of the country. Instead, he betrayed his opposition party friends for his own selfish desire, then to cover his bad name and reputation he come up with this third option to renew his damaged status. This is clearly shown both in his action of withdrawing himself from the politics very quickly and the poor commitment he and his supporters showed to disseminate their view to be considered as an option by the people and other parties. To say it in short and precise way, what Ato Ledetu and his party tried to do after the 1997E.C election was to restore the bad image of their personality and party. I am really sorry to say that but the is the bald truth.

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?

የማካቬሌ ፍልስፍና

የፍቅር ትርጉሙ