የኢትዮጵያ ታሪክና የኦሮሞ ህዝብ
በግርድፍ የዳሰሳ ጥናት ከአምስት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች አራቱ የኢትዮጵያ ታሪክ የባለቤትነት ስሜት የለሌላቸው ሲሆን ከአምስቱም አምስቱ በኢትዮጵያ ታሪክ የኦሮሞ ህዝብ በተለዬ መልኩ እንደበተደለ
ይሰማቸዋል። በእነዚህ ወገኖች በስፋት ሲነሳ የምሰማው መከራከሪያ አሳብ ሲጨመቅ ሀ/ የኦሮሞ ህዝብ በባለፉት ስርአቶች በእኩልነት የመሳተፍ እና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ተጠቃሚ የመሆን መብቱ ከሌሎች ህዝቦች በተለዬ ተነጥቋል ለ/ የኦሮሞ ህዝብ በባለፉት ስርአቶች የህልውናው መሰረት የሆነውን መሬት ተነጠቋል የሚል ነው። እነዚህ መነሻዎች አሁን ድረስ ባለው አገራዊ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አላቸው ።
እኔ ገለልተኛ ሆነህ በጉዳዩ ላይ አሳብ ስጥ ብባል ልሰጥ የምችለው አሳብ ይሄ ነው። በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ህዝብ በተለዬ መልኩ የተበደለበት የታሪክ ሂደት የለም። በኢትዮጵያ ታሪክ በነበሩት ስርአቶች ሁሉም ህዝብ ተመሳሳይ በደል አሳለፏል። በተለምዶ ከባለፉት ስርአቶች ተጠቃሚ እንደሆነ የሚታማው የአማራ ህዝብ አሁንም ድረስ በድህነት አረንቋ የሚማቅቅ፣ ያልተማረ፣ የባለፉት ስርአቶች በደሎች የፈጠሯቸው ማህበረሰባዊ ችግር የተተበተበ ነው። የትግራይ ህዝብ የሚባለውም ቢሆን ከባለፉት ስርአቶች በተለዬ መልኩ ተጠቃሚ የሆነበት ሁኔታ የለም። የተቀረው ህዝም በተመሳሳይ ሊወሰድ የሚችል ነው። ስለዚህ በባለፉት ስርአቶች የነበረው በደል ተመሳሳይ ሆኖ ልዩነቱ የተፈጠረ በደሉን ያስተናገዱበት ስሜት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የማነሳው ጥያቄ የባለፉት ስርአቶች ስህተት መፈፀማቸውን ተማምነን ስናበቃ በባለፉት ስርአቶች የተፈፀሙት ችግሮች ዛሬ ላይ ይስተካከሉ ሲባል የሚፈጠረው ልዩነት እርስ በርሱ የሚጣረስ መሆኑ ነው። አሳቡ በአጭር ሎጂክ ሲቀርብ የባለፉት ስርአቶች ስህተት ፈፅመዋል ከተባለ ስህተቱን ዛሬ ለማስተካከል አንድ መሆን ነው። የባለፉት ስርአቶች የፈፀሙትን ስህተት ዛሬ ላይ ለማስካከል ልዩነት ከተፈጠረ የባለፉት ስርአቶች ትክክል ነበሩ ወደሚለው የሚወሰድ ነው። ስለዚህ ምርጫው አንድም የባለፉት ስርአቶች የፈፀሙትን ስህተት ዛሬ ላይ ማስተካከል ወይም ዛሬ የሚስተካከል ችግር የለም ከተባለ የባለፉት ስርአቶች ትክክል መሆናቸውን መቀበል ሊሆን ነው ማለት ነው።
በሁለተኛ ደረጃ ሊታይ የሚችለው ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ በባለፉት ስርአቶች መሬቱን ተነጥቋል የሚለው መከራከሪያ ነው። ይህ መከራከሪያ ብቻውን አይደለም። መከራከሪያውን ተከትሎ የሚመጣው ጥያቄ በባለፉት ስርአቶች የተነጠቀው መሬታችን ዛሬ ይመለስ የሚል አሳብ የያዘ ነው። እዚህ ላይ የሚሰማኝ በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መሬቱ ያልተነጠቀበት ህዝብ እንደሌለ ሁሉ ከሌላ ህዝብ ላይ መሬት ያልነጠቀ ማህበረሰብ አለመኖሩ ነው። በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ የኦሮሞ ህዝብ መስፋፋት በስፋት የነበረበት የጎላ ታሪክ ነበረ። መሬት ተነጠቅን በሚለው መሰረት የሚኬድ ከሆነ በዚህ የኦሮሞ መስፋፋት ማህበረሰባዊ ሂደት የኦሮሞ ህዝብ እንደ ስርአት መሬት የነጠቃቸው ህዝቦች ነበሩ። በኢትዮጵያ ታሪክ አንዱ ነጣቂ ሌላው ተነጣቂ ሳይሆን እርስ በርሱ እየተነጣጠቀ የመጣ በመሆኑ ለብቻው የሚወነጀል አይኖርም። ስለዚህ ብቸኛው አማራጭ ዛሬ ላይ መሬቱን በጋራ ለመጠቀም መስማማት ብቻ ነው። በእኔ እምነት አሳቡን በቀረበበት መንገድ አይቶ አመለካከትን ማሻሻል በጋራ አገር ላይ በእኩል ተሳትፎ ፍትሀዊ ተጠቃሚ መሆን የሚቻልበትን ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመመስረት የሚያግዝ ይመስለኛል።
Posted by EthioSophi Admin

ኦሮሞ
ReplyDelete