ታማኝነት ምንድነው?

ታማኝነት እውነተኛ ነኝ በሚል በአንድ ጉዳይ ላይ ለረጅም ጊዜ መጣበቅ ሳይሆን ከሁኔታዎች ጋር የሚናበብ ኃላፊነት የተሞላበት ማስመሰልም ጭምር ነው። ሌሎች ላይ የእምነት ስሜትን መፍጠር ካልቻልክ የአንተ ታማኝነት ከንቱ ነው። እምነት የሚፈጠረው ደግሞ ለመምስል ያስገደደህን ሁኔታ በግልፅ በማሳየት ነው።



ሁልጊዜ እውነተኛ መሆን አይቻልም። የሚቻለው ከውጤት ጋር የሚመጣጠን መሆን ነው። ሁኔታዎች በፍጥነት በሚለዋወጡበት አለም አንዴ የሆንከውን ሆነህ መቀጠል አትችልም። የአንተን መሆን ከሁኔታዎች ጋር ለማስታረቅ ትገደዳለህ። ይህ ማለት ከሁኔታዎች ጋር መመሳሰል ማለት ነው። በሌላ አነጋገር ከሁኔታዎች ጋር መመሳሰል ማለት ማስመሰል ማለት ነው።  ውሸት አልወድም ማለት በራሱ ውሸት ነው። እውነት ራሷ የሚመስላትን እንጂ የሚሆናትን አትወድም። መሆን የቻልከውን ሆነህ እውነትን ማስመሰል ከቻልክ እውነተኛ ማለት እሱ ነው።

Posted by EthioSophi Admin

Comments

Popular posts from this blog

የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?

የማካቬሌ ፍልስፍና

የፍቅር ትርጉሙ