የአምላክ ታሪክ
አምላክ የሚለው ቃል ሁሉን ማድረግ የሚችል፣ ፍፁማዊና ዘላለማዊ ህልውና ያለው የሁሉም ነገሮች ምንጭ የሆነ አካል የሚለውን ፅንሰ አሳብ በሚወክል መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ለአምላክ የተሰጠው ገፅታ አምላክ የወንድ ጾታ ያለው፣ ሩህሩህ፣ መሀሪ ፣ ደግ የመሳሰሉትን የሰው ባህሪያት በማስቀመጥ ከሰው ልጅ ጋር በሚመሳሰል መልኩ ሲቀመጥ በሌላ መልኩ ደግሞ አምላክ የሰው ልጅ የያዛቸውን ባህሪያት ዉጪ የሆኑ ባህሪያት ባለቤት እንደሆነ የሚያስረዱ ገጽታችም ይቀመጣሉ፡፡
ለምሳሌ የጥንት ግሪካውያን አምላክን በእነስሳትና በተለያዩ ፍጥረታት ገፅታ በመሳል የሚያመልኩ ሲሆን ሌሎች ጸሀይን ወይም ጨቃን እንደ አምላክ በመውስድ ሲያመልኩ ቆይተዋል፡፡ በቁጥር ደረጃ አምላክ አንድ ነው ከሚሉት የአይሁድ እምነት ተከታዮች ጀምሮ ሶስት አምላክ እንዳለ እሰከሚያምኑት የክርስትና እምነት ተከታዮች ሊሄድ ይላል፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ አምላክን በሚመለከት የነበሩ አስተሳሰቦችን ታሪካዊ ሂደት በማጥናት ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

ከጥንታዊ ግሪካዉያን በፊት የነበሩ ማህበሰረቦች የራሳቸው የአምላክን ገፅታ ያላቸው ቢሆንም እኔ ታሪካዊ ጥናቱን የምጀምረው ከማውቃቸው ጥንታዊ ግሪካዉያኑ ፈላስፋዎች በመነሳት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በጥንት ግሪክ ነበሩ ፈላስፋዎች ተፈጥሮን ለማጥናት የተጠቀሙባቸው ትንታኔዎች የአምላክ ገፅታን ለመገንባት ግልጋሎት ላይ ዉለዋል፡፡ ለምሳሌ ለሔራክልተስ ሁሉም ነገር ተለዋዋጭ መሆኑ፣ የሁሉም ነገር ምንጭ እሳት እንደሆነና ሁሉም ህልውናቸውን ያገኙት ከእሳት እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ለፓራሜንደስ የሁሉም ነገሮች ለውጥ በገልጽ ሊታይ የሚችል መሆኑን ሲያስቀምጥ አናክዛጎራስ መንፈስ እና ቁስ የሚባሉ ሁለት አይነት እውነታዎች መኖራቸውን በማስቀመጥ አምጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት አናክዛጎራስ መንፈስ ያለው እውነታ የአለማትን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር ኃይል እንደሆነ ያምን ነበር፡፡ ፓይታጎሪያንስ የሚባሉት ከአሁኑ የሀይማኖት ልምምድ ጋር በእጅጉ የሚመሳሰል ሀይማኖት ነበራቸው፡፡ ለፓይታጎረሲያኑ እውነት ማለት ቁጥር ናት፡፡ በዚህ መሰረት አምላክን ምናባዊ ቅርጽ ያለው አድርገው የሳሉበት ገጽታ ኋላ ላይ የፕላቶ ፍልስፍና ላይ ተፅዕኖ አድርጎ ነበር፡፡ በሌላ በኩል አቶሚስት ተብለው የሚታወቁት ሊስፐስ እና ዴሞክረቲስ እውነት የቁስ (matter) አድርገው ያስቀመጡ ነበር፡፡ እነዚህ ጥንታዊ አስተሳሰቦች ታዲያ የአምላክን ገፅታ ለማሳል የራሳቸው የሆነ አስተዋፅኦ ነበራቸው፡፡
የአምላክን ገፅታን በሚመለከት አሁን በዘመናችን ካሉ ሀይማኖቶች ጋር በእጅጉ የሚመሳሰል ገፅታን የሳለው ፕሌቶ ነው፡፡ የፕሌቶ ፍልስፍናዎች በዛ ላሉ የክርስትናና እስልምና ሀይማኖቶች የዶክትሪን ምንጭ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ፕላቶ ለአምላክ የሰጠው ገፅታ አምላክ ፍፁምና ምጡቅ የሆነ ፣ በሆነ አለማት ላይ የሚኖር የነገሮች ሁሉ ምንጭ አድርጎ ነበር፡፡ ፕሌቶን ተከትሎ የመጣው ፈላስፋ አርስቶትል አምላክን “የለውጥ ምንጭ” አድርጎ በመሳል አስቀምጧል፡፡ የሁሉም ነገሮች ምንጭ የሚያንቀሳቅስ ግን የማይንቀሳቀስ ( Unmoved mover) አደርጎ ያስቀምጣል፡፡
ከፕሌቶና አርስቶትል ቀጥሎ የአምላክን ገጽታ በመሳል የጎላ ሆኖ ያገኘሁት ፈላስፋ ፕሎቲኒየስ ነው፡፡ እንደ ፕሎቲኒየስ እምነት አምላክ አንድ ነው፡፡ አምላክ ማለት የማይለወጥ፣ ዘላለማዊ እና ፍጹማዊ ህልውና ያለው፣ በሰዎች ግንዛቤ ሊደረስበት የማይችል አካል ነው፡፡ ፕሎቲነስ እንደሚለው ቁስና መንፈስ በለውጥ ሂደት ተፅእኖ ስር ስለሆኑ አምላክ የተሰራበት ንጥረ ነገር ከነዚህ ዉጪ ነው፡፡ የአምላክን ባህሪ በትክክል የሚያስረዳ የሰው ቋንቋ ስሌለ አምላክ ይህ ነው ተብሎ ሊወሰን አይችልም፡፡ በግሌ የተረዳሁት ከፕሎቲነስ በፊት የነበሩ የጥንት ግሪካዉያን ፈላስዎች የአምላክን ገፅታ የሚስሉበት መንገድ ከሀይማኖታዊ አላማ ወጣ ብለው ከተፍጥሯዊ ትንታኔ አንጻር ብቻ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የአዉሮፓ በክርስትና ሀይማኖት መወረርን ተከትሎ አምላክ የሚሰጠው ገጽታ ለክርስትና ሀይማኖት ዶክሪን በሚመጥን መልኩ እየሆነ በመምጣት ሀይማኖታዊ ትንታኔው ጎልቶ ወጣ፡፡
ከዚህ አንፃር በክርስትና ዶክትሪን ቀረፃ የጎላ ሚና የነበረው ሰው አውግስጢኒዮስ ነው፡፡ አውግስጢኒዮስ የፕሌቶና የፕሎተኒዮስ ተፅዕኖ የጎላበት ፈላስፋ ቢሆንም ከሁለቱ በተለየ መልኩ የአምላክን ገጽታ ለመገንባት ጥረት አድርጓል፡፡ እንደ አውግስጢኒዮስ እምነት አምላክ በራሱ ለራሱ የሆነ ህልውና ያለው፣ በጊዜና በቦታ ማይገደብ ፣ ፍጹማዊ የሆነ አካል ነው፡፡ አውግስጢኒዮስ እንደሚለው አምላክ ማለት እውነት ነው፡፡ በመሆኑም አምላክ በእያንዳንዱ ሰው ልቦና ውስጥ የተቀረፀ ህልውና ነው፡፡ ሁሉም ነገሮች የአማላክ መገለጫዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከአምላክ ጋር ተመሳሳይ ባህሪ የላቸውም፡፡ አምላክ ሁሉንም ነገሮች የፈጠረው ከባዶ በመነሳት ሲሆን ይህም አማላክ ሁሉን ነገር የፈጠረው አስቀድሞ ከነበረ ነገር ነው የሚለውን ለማፍረስ የተሰጠ ምላሽ ተድርጎ ይወሰዳል፡፡ ከአውግስጢኒዮስ ቀጥሎ የሚመጣው ፈላስፋ አንሰለም ነው፡፡ አንሰለም አምላክን የሳለበት ገፅታ ከአውግስጡኒየስ የተለየ ባይሆንም የአምላክን መኖር ለማረጋገጥ ያስቀመጠውና እስከአሁንም ድረስ የሚደነቅለት ትንታኔ አለው፡፡ አንሰለም እንደሚለው “የምረዳው ለማመን አይደለም፡፡ የማምነው ግን ለመረዳት ነው”፡፡ በዚህ መሰረት አንሰለም አምላክን በአግባቡ ለመረዳት የመጀመሪያው ደረጃ ለመረዳት ማመን ይላል፡፡ እንደ አንሰለም አሳብ የአምላክን መኖር ለማጋገጥ ከምንረዳቸው ነገሮች ጋር በማነፃፀር ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ይህ ማለት “ጥሩ” የምንለው ነገር ካለ እኛ “ጥሩ” ካልነው የበለጠ ሌላ ፍፁማዊ “ጥሩ” ሊኖር እንደሚችል መቀበል ማለት ነው፡፡ በዚህ መሰረት በገሀዱ አለም በተለያየ ደረጃ የምንረዳቸው ነገሮች ሁሉ ፍጹማዊ የሆነ ደረጃ አላቸው ማለት ነው፡፡ ይሕ ፍፁማዊ አካል ደግሞ አምላክ ነው፡፡
ከአንሰለም በኋላም በአምላክ ገጽታ ግንባታ ዙሪያ የተረደጉ ጥረቶችየቀጠሉ ሲሆን ለጊዜው እዚህ ላይ እንገታና የሻይ እረፍት እንወጣለን፡፡ በተነሳው አሳብ ላይ ጥያቄ ያለው ካለ እቀበላለሁ፡፡
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment