ድብቅ በቀል
ድብቅ በደል የሚታወቀው ተበዳይ በዳይን መልሶ ሲበድለው ነው።
በግልፅ ይቅር የሚሉህን በልብህ አክብራቸው። በድብቅ የሚበድሉህን በአደባባይ አዋርዳቸው።
በድብቅ መበደል ከይቅርታ ይልቅ የሚቀናው በአደባባይ ለመበደል ነው።
አንዳንድ ሰው ጓደኛ የሚሆንህ እሱ በሚፈልገው ሁኔታ ነው። እሱ ሲፈልግ ይቀርብሀል። ካልፈለገ ይርቅሀል። እሱ በሚፈልግበት መልኩ ጓደኛ ይሆንና እሱ በሚፈልግበት ሁኔታ ስትፈልገው አንተ በምትፈልገው መገኝት አይፈልግም። እሱ በሚፈልገው እዲገኝ መፈለግ እሱ ካልፈለገ ስህተት ነው። ይህ አንዱ ድብቅ በደል ነው።
ጓደኝነት ሁለት አይነት ጉድኝት ነው። አንደኛው አካላዊ ጉድኝት ፣ ሁለተኛው የስሜት ውህደት። ከአካላዊ መሰባሰብ ይልቅ የስሜት ውህደት ንፁህ ለሆነ ጓደኝነት አስፈላጊ ነው። አንተ ስሜትህን የሰጠኸው በአካሉ ከአንተ ተገናኘ። አንተ ስሜትህን ሳስት እንድትሰጠው አድርጎ የራሱን ስሜት ከሰሰተ ከዚህ በላይ ክህደት ምን አለ?
በጓደኝት ውስጥ የሚኖርህ የተሳትፎ ዋጋ እየቀነሰ ከሄደ የአንተ በጓደኝነቱ ውስጥ መቀጠሉ አስፈላጊነት ተሸረሸረ። በጓደኝነቱ ውስጥ በተቻለ መጠን ተሳትፎህን ዝቅ ላለማድረግ ሞክር። ከጓደኞችህ ጋር ተመጣጣኝ ተሳትፎ ማድረግ ካልቻልክ አንተ ጓደኛቸው ሳትሆን አሸንጉሊታቸው ነህ።
እሱ በሚፈልገው መልኩ ሁልጊዜ የምትገኝለት ጓደኛህ አንድ ቀን አንተ በምትፈልገው መልኩ ለመገኘት የማይፈልገውን መሆን ካልፈለገ፣ እሱ የአንተ ጓደኛ አንተ ደግሞ የሱ አሻንጎሊት ነህ።
ከአንተ ምንም አልፈልግም ብሎ ሳይፈለጉ መፈለግ በራሱ የሆነ ነገር መፈለግን የሚያሳይ ፍላጎት ነው።
ሌላው ድብቅ በደል ምንድነው? እሱ ሲፈልግ በብዙ ቀርቦህ ፣ እሱ በቀረበበት ቀረቤታ ለመቅረብ ስትፈልገው የሚርቅህ ሰው በድብቅ እየበደለህ ነው።
በጓደኝነት ውስጥ ከባድ በደል የሚፈፀመው በግልፅ ሳይሆን በድብቅ ነው። የጓደኛን ስሜት ሳይጠብቁ በራስ ስሜት ብቻ ትክክል መሆን ስህተት የሆነ ድብቅ በደል ነው።
ከጓደኝነት አላስፈላጊው ነገር በማያስፈልግ ወቅት አስፈላጊ ሆኖ በሚፈለግብት ጊዜ ያለመፈለግ ስሜት ነው።
እሱ ከአንተ የሚፈልገውን ያህል የስሜት ውህደት አግኝቶ አንተ በተመጣጣኝ የእሱን ስሜት ስትፈልግ የሚገፋህ ሰው ጓደኛ የሆነህ ጉድጓድ እስኪገኝ ነው። ከዛ በኋላ ስሜትህን ወስዶ አካልህን መግፋት ነው።
አንተ ሳትፈልግ እሱን እንድትደው አድርጎ የማይወድህ ሰው ባያጠቃህም ጠላትህ ነው።
በጓደኝነት ውስጥ ያለህ ሚና ዋጋ የሚጠፋው ከጓደኝነት በታች የስሜት ማረጋፊያ አሻንጉሊት ከሆንክ ነው። ይህ ትልቅ ድብቅ በደል ነው።
አንተ የጓደኝነቱ ህልውና ቀጣይነት ላይ ምንም ተፅእኖ ከሌለህ አንድ ቀን ፍላጎት ብቻ ከጓደኝነት ውጪ ነህ። አንተ መጨረሻውን መወሰን የማትችልበትን ጓደኝነት መጨነቅ የለብህም። ተጨነቅክም አልተጨነቅክ አንተ ሳትለየው እሱ መለዬቱ አይቀርልህም።
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment