የፍቅር ትርጉሙ

የፍቅር ትርጉሙ ከአካል ህብረት፣ የስሜት ውህደት፣ ከሰውነት ድክመት የመንፈስ ብርታት ነው። በስጋ ቢዝልም ፣ ሰው በስሜቱ ብርታት ስጋን የሚያክም ነው።



ፍቅር የአካል ምቾት፣ የሀብት ሙላት አይደለም። የህሊና ውህደት ነው።የስሜት ሙላት ነው። ሲመቸው ብቻ የሚኖር ድንጋይ ነው። ድንጋይ ደልዳላ መሬት ካገኘ፣ አድቦ ይቀመጣል። አይንከባለልም። ከሌላ ድንጋይ ጋር አይጋጭም። ስሜት ግን ሁሌም ምቾት አለው። ቢቆረቆርህም ፍቅር ትራስህ ነው። በጭንቀትህ ጊዜ ፣ አካልህ ሲደክም ምቾትህ ፍቅር ነው።

የቦታ ምቾት ሰው አያዋድድም። ሰው በአካሉ ባይመቸው ካፈቀረው ጋር ይኖራል። የህሊና ምቾት፣ የፍቅር ትራስ ነው። ልብ ላይ ተኝቶ የሚያርፍበት። ሰው በህሊናው ከተለየ፣ የፍቅር ጠንቅ ነው። እውነታኛ ፍቅር የሚገኘው፣ ከአካል ምቾት ሳይሆን፣ ከህሊና ውህደት ነው። አንቺ ትብሽ፣ አንተ ትብስ በአካል ከመተቃቀፍ በላይ የስሜት መተሳሰብ የፍቅር ትርጉም ነው።

Comments

Popular posts from this blog

የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?

የማካቬሌ ፍልስፍና