የህይወት መፍትሄው የስሜት ለውጥ ነው።
የህይወት መፍትሄው ችግር ማጥፋት ሳይሆን አንዱን ችግር በሌላኛው ችግር ተክቶ የስሜቱን ትርጉም በመለዋወጥ ነው። የበሽታ መድሀኒቱ በሽታውን ማጥፋት አይደለም። መድሀኒቱ በሽታን በሌላ በሽታ ተክቶ፣ የበሽታውን ስሜት መለወጥ ብቻ ነው።
አንድ መድሀኒት የሚወፍስህ በሽታህን በማጥፋት ሳይሆን ስለበሽታህ የሚሰማህን ስሜት በመቀየር ነው ። ሳይድ ኢፌክት ልብ ይሏል!
ህይወት እውነት የሌላት የስሜት ትርጓሜ ከሆነች እውነቷ እንደ ትርጉሟ ነው። ችግር ሆኖ የሚሰማህ ምን ጊዜም ችግር ነው። ችግሩ የመፍትሄው ስሜት ሲጠፋ ብቻ ነው።
ህይወት ልሙጥ ናት። በህይወት ውስጥ ችግርም ፣ መፍትሄም የለም። የችግርና ድሎት ልዩነቱ ምንጭ ከኑሮው ሳይሆን የነዋሪው ስሜት ነው።
የህይወት ሂደት ችግር ፈጥሮ ችግር የመደበቅ ሂደት ነው። መፍትሄው ችግርን ማስወገድ ሳይሆን ችግሩን በራሱ ችግር እንዳልሆነ የሚወሰድ ስሜትን የመፍጠር ሂደት ነው።
በህይወት ውስጥ ትልቁና አስቸጋሪ ነገር ችግር መኖሩ ሳይሆን ለችግሩ የመፍትሄ ስሜት መፍጠር አለመቻል ነው። የህይወት ትርጉም የሚወሰነው የችግርና መፍትሄ ቅንብር ከሚፈጥረው የስሜት ለውጥ ነው። ዋናው ችግር ህይወት ችግር አጥታ ስሜቷ ሲጠፋ ነው። የችግር ስሜት የሌለው ህይወት የቁም ሞት መኖር ነው።
የህይወት መፍትሄ የሚባለው ችግር መፍታት ሳይሆን ችግር መደበቅ ነው። ችግር እንዳለ ካልተሰማህ መፍትሄው እሱ ነው። መፍትሄው ቢኖርም ስሜቱ ካልጠፋ ሁልጊዜም ችግር ነው።
በተለያዬ ሁኔታ ውስጥ መኖር የሚያሳየው የአኗኗር ዘይቤ ልዩነትን እንጂ የኑሮ መበላለጥን አይደለም። ችግርም መፍትሄም የህይወት ትርጉም ነው። ህይወት ትርጉም የምታጣው ምንም ጣዕም ጠፍቶ ስሜት አልባ ስሜት ሲፈጠር ብቻ ነው።
በጥሩ ስሜት መኖር በመጥፎ ስሜት ከመኖር በላይ የተሻለ የመሆኑን ያህል በመጥፎ ስሜት መኖር ደግሞ ምንም ያልሆነ ስሜት ውስጥ ከመኖር እጅግ የተሻለ ነው።
በህይወትህ የተፈጠረን ችግር ከተደበቅከው ትልቅ መፍትሄ ነው። ችግሩ የተደበቅክበት መፍትሄ አፍዝዞ አስቀርቶህ የችግር ስሜቱ ሲደበቅብህ ነው።
ምንም ቢሆን አፈር ነህ። ወደ አፈርም ትሄዳለህ። ምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆን በራሱ ችግር ነው። ብትቀመጥ ችግር፣ ብትቆም መከራ ነው። ስትራመድ ችግር፣ ስትሮጥም ችግር ነው። የሚያስደስተው ነገር ትልቁ መፍትሄው ያንኑ ሂደት መልሶ መድገም መሆኑ ነው። መቀመጥ ችግር ሲሆን መቆም መፍትሄ ነው። መቆም ችግር ሲሆን መፍትሄ መራመድ ነው። የችግር መፍትሄው ፣ ችግሩን እየለዋወጡ፣ በተለዬ ስሜት ደጋግሞ መኖር ነው።
የህይወት ፈተና የገሀዱ አለም እውነታ ሳይሆን የስሜት ሁኔታ ነው። ሁኔታዎች እውነት ሳይሆኑ የስሜት ትርጉሞች ናቸው። የሚለዋወጡት በቦታና ጊዜ ለውጥ ሳይሆን በስሜት ለውጥ ነው። የህይወት ፈተና ለማምለጥ ቦታ የምትቀይረው የተለዬ ህይወት ለመኖር ሳይሆን ስለህይወት የሚሰማህን ስሜት ለመለወጥ ብቻ ነው።
በህይወት ውስጥ ለሚያጋጥም ችግር መፍትሄ የለም። ለችግሩ መፍትሄው አንድ ብቻ ነው። ይኼውም ችግሩን ችግር አድርጎ ሊወሰድ የማይችል የስሜት ለውጥ ነው።

Comments
Post a Comment