የታሪክ ሽሚያ

በቅርቡ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን  ታሪክ ተጠያቂነትን በሚያከፋፍል መልኩ ቀምሮ አቀረበ። የታሪክ ትንተናው ዛሬ ያለችው የተጎሳቆለች አገር የኔ ውጤት ሳትሆን  ከባለፉት ስርአቶች እየተጎተተ የመጣ ችግር የፈጠራት እንደሆነች እወቁልኝ ነው። በእርግጥ እኔም እንደማምነው የኢትዮጵያ ችግር ፈጣሪ ኢህአዴግ ብቻ አይደለም። የዛሬው ችግር ትናንት መሰራት የነበረባቸው የቤት ስራዎች ባለመሰራታቸው የመጣ ችግር ነው። ይሁን እንጂ ታሪክ የመሻማት አይነት ነገር እያየሁ ነው።



አስተውላችሁ ከሆነ አላውቅም። የአማራ ተወላጆቹ የአፄ ሚኒሊክ ገፅታ በኢትዮጵያ ታሪክ ገኖ እንዲወጣ ይፈልጋሉ።  አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ደግሞ አፄ  ዩሀንስን ለማግነን በሚመስል መልኩ ነጥለው ማውጣት ጀምረዋል። ኦሮሞዎቹም እንዲሁ አሉን የሚሏቸውን። በዚህ የታሪክ ሽሚያ መሀል አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ታሪክ የእርቦ ቆሎ ቢሆን ኖሮ ተሻምተው ጨርሰውብን ነበር። ደግነቱ ታሪክ ትናንት ብቻ ሳይሆን ነገም ይፈጠራል። ብሔር - ብሔረሰቦቻችንን ግን ታዘብኳቸው። ኧረ! ባካችሁ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ የሆነ አዲስ ብሔር ለኛም ፍጠሩልን??!

Posted by EthioSophi Admin

Comments

Popular posts from this blog

የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?

የማካቬሌ ፍልስፍና

የፍቅር ትርጉሙ