የፖለቲካ ትግል መለኪያ
የፖለቲካ ትግል ስኬት የሚለካው በፈጠረው የብዙሀን ግርግር ሳይሆን በብዙን ላይ ባመጣው የአስተሳሰብ ለውጥ ነው። ስር የሰደዱ ችግሮችን ወቅታዊ በማድረግ የተለየ ቀለም ሰጥቶ የብዙሀንን ግርግር መፍጠር የፖለቲካ ትግል ደረጃ የሚመጥን አይደለም።

ማንኛውንም አይነት ጥያቄ መመለስ የሚቻለው በብዙሀን ግርግር በማዋከብ ሳይሆን በሰከነ መልኩ ህግና ስርአትን በማክበር በሚከናወን ሰላማዊ ትግል ነው። ከግርግር የሚገኘው ዋናው ነገር የሚፈለገው ጥያቄ ተቀልብሶ በመሀል በሚፈጠረው ግርግር ጋጠወጦች በሚፈጥሩት ስህተት የንፁሀን ደም መፍሰስ ይሆናል። ግርግርን መሰረት አድርጎ የሚከናወን የፖለቲካ ትግል ምንጊዜም ቢሆን ዜጎች የተነሱበትን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የንፁሀን ዜጎችን ደም የሚጠይቅ ይሆናል። የዜጎች ደም መፍሰስ ልብ የሚነካ አሳዛኝ ክስተት ቢሆንም የስሜት ነውጥ በፈጠረው ያልተገራ እንቅስቃሴ ላይ ከመሳተፍ መቆጠብ የራስን ደህንነት ከማስጠበቅ አልፎ የአገርንም ሰላም ለመጠበቅ የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለው ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።
ከምንም በላይ የፖለቲካ ትግል ውጤታማነት የሚለካው ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ በሚደረጉ የብስለት እንቅስቃሴዎች ላይ የተመሰረተ ሲሆን መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባቱ ብልህነት ይመስለኛል። ሀይማኖቴን ላስጠብቅ፣ መብቴን ላስከብር፣ አምባገነን መንግስትን ልታገል በሚል ግልብ ስሜት ተገፋፍቶ ጥንቃቄ በጎደለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ራስን በእሳት ከማያያዝ ተለይቶ አይታይም። የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር እንዲሉ በአለማዊውና በመንፋሳዊው ገዥዎች መካከል ያለውን ልዩነት ባገናዘብ መልኩ የሚነሱ ጥያቄዎችን መቃኘት ያስፈልጋል። ከሰላም ውጪ ዋጋ የምንከፍልለት ትግል የለም። ከሰላም ውጪ የምንፈልገው ህይወት የለም። በሰላም ውስጥ ሆኖ የሰላምን ጣዕም ለመረዳት የመከራን መራራ ጣዕም መቅመስ አስፈላጊ አይደለም። ቅድሚያ ለሰላም ቦታ እንስጥ!

Comments
Post a Comment