ሞት
ሞት ማለት ነብስህ ከአካል ተለይታ ወደ ሰማዬ ሰማያት የምትሄድበት ዘላለማዊ መለየት ነው። እንቅልፍ ማለት ደግሞ ነፍስህ ከስጋህ ተለይታ ከጣሪያው ላይ የምትሆንበት ጊዜያዊ መለየት ነው። ጧት ስትነቃ ዱብ ትልና ከስጋዋ ትቀላቀላለች። ስትተኛ ነብስህ ጣሪያ ላይ ሆና ትታዘብሀለች።
ስትሳሳት ቅዥት፣ ስትመኝ ህልም ታወርድልሀለች። ነብስ እንደ ስጋ እንቅልፍ የላትም። ህይወቷ ቆሞ መኖር ነው። ካረፈች ትሞታለች። ስጋ ደካማ ነው እረፍት የሚፈልግ። ስጋ ሲከፋው እረፍት ይመኛል። ነብስ እረፍት የምትፈልገው ሲመቻት ነው። ስትጠግብ ታርፍና፣ በቅብጠቷ እረፍት ትሞታለች። የስጋ እረፍት ለመኖር ነው። የነብስ ግን ለመሞት።
ስጋ ነብስን የሚይዝ ብርጭቆ ነው። ነብስ ትኩስ ውሀ ሆና እያቃጠለች ታቀልጠዋለች። ስጋም ማታ በእንቅልፍ ቀልጦ አልጋ ላይ ከነብስ ይሰናበታል። የቀን ውሉ የህይወት ምጣድ ነው፣ ነብስ ስጋን ለመምራት፣ ስጋም በራሱ ለመመራት የሚታገሉበት። ነብስ ስጋን የምትለበልብበት። ስጋ በነብስ እሳት የሚቀልጥበት። ዝልፍልፍ የሚልበት። ስጋ ከነብስ ጋር የሚታገልበት። ነብስ ገዢ ለመሆን፣ ስጋ ለማመፅ የሚበስሉበት። የዛሬ ህልም የነገ እንጀራ ነው። በህልም ተቦክቶ፣ በእውነት የሚጋገርበት። ነብስ አብስላው፣ ስጋ የሚበላው።
ነብስ ለስጋ ስትል እንደ ጎሽ ተወጋች። ራሷን አስርባ፣ ስጋ አየተመገበች። የስጋ ረሀብ በነብስ ይታገሳል። ነብስ ስትራብ በምን ይታገሳል!? ስጋ የሚርበው የራሱን ስጋ ነው። ነብስ የምትራበው ግን የሌላን ፍቅር ነው። በደል፣ የፍትህ ረሀብ። ሞኝነት፣ የጥበብ ረህብ። ሀዘን የደስታ ረሀብ። ስጋ ስጋን ሲራብ፣ ነብስ ፍቅርን ትራባለች። ሌላው ካልመገባት፣ ራሷን በልታ ትጠፋለች። የፍቅር ምግብ ስታጣ፣ የራሷን ጥላቻ ትበላለች።
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment