ይቅርታ
ይቅርታ በራሱ ምንም ነው። የይቅርታ ዋጋ የበደል መኖር ነው። በስህተት በደል የይቅርታ ዋጋ በገንዘብ ቢተመን የትዬለሌ ነው። ከምንም ነገር በላይ ይቅርታ የሌለው ስህተት ቢኖር ይቅርታን አጥፍቶ እንደተበደሉ በበደል መኖር ነው።
ይቅርታ ከሌለ በደል ትርጉሙን ቀይሮ ይቅርታን ይበድላል። በዚህ ጊዜ በደል እውነት ሆኖ መበደል በራሱ ትክክል ይሆናል።
በበደል የተሞላውን ልብህን በጥላቻ ቂም አትዝጋው። ይቅርታ ከልብህ ቢወጣም በትዝታ ቅርበት ከደጅህ ይሆናል እንጂ ቂም አያባርረውም። ስለዚህ በደል የገባበትን የልብህን በር በቂምህ አትዝጋው። ብዙ ጊዜ በቂም የተዘጋው ልብህ ቆስሎ የሚደማው በይቅርታ ግፊት ልብህ ሲሰበር ነው።
ይቅርታና በደል አንድ ናቸው። ጥንድ ሆነው በአንድነት መኖር ግን አይችሉም። ይቅርታ አንድ ነው። በደልም አንድ ነው። አይደጋገሙም። በደል ሲደጋገም ራሱን ያጠፋል። በይቅርታ የተደገመ በደል በፍቅር ይሟሟል። ይቅርታ ሲደጋገም ራሱን ያበዛል።ይቅርታ ሲበዛ የበደል ስቃዩ ደርቆ ይረግፋል።
ስትበደል እንደምታዝን ሁሉ በይቅርታ ጊዜ የደስታ ስሜት ከሌለህ አንተ ራስ በደለኛ ነህ። ለማይጠፋ በደል ራስህን የበደልክ።
መራራ በደል ባይኖር ኖሮ ጣፋጭ ይቅርታ ባልኖረ ነበር። በደል በቂም ህይወት ለዘላለም ዘላለም መኖር ቢችልኳ በይቅርታ ሀይል ከቂም ላይ ይሞታል። ቂም ዘላለም ሆኖ ይቅርታ ሲጠፋ ፣ በደል ትርጉሙን ለውጦ ፣ መበደል በራሱ ካሳ ሆኖ ያልፋል።
ግማሽ አካሏ በኢ-ፍትሀዊ በሆኑ ነገሮች የተሞላች ህይወት ውስጥ እየኖርክ በህይወትህ ውስጥ አንድ በደል ብቻ የምትጠብቅ ከሆነ ተሳስተሀል። የምትወደው ሰው ተደጋጋሚ የበደል እድል መስጠት የሚጠቅመው በብዙ በደሎች ከመጠቃት አስቀድሞ ብዙ በደሎችን በአንድ ይቅርታ አጥቅቶ ማስወገድ ቀላል በመሆኑ ነው።
የሰው ልጅ ህይወት የስሜት ትርጉም ነው። ሊቅ ሆኖ ቢጠበብ፣ በእውቀት ቢራቀቅ፣ በጥበብ ቢሞላ ገዥው ግን ስሜት ነው። አንድ እና አንድ ሲደመር ሁለት ነው ብለህ በጥፊ ብትመታው ፣ ካስተማርከው እውነት ይልቅ እሱን የሚገዛው የጥፊው ስሜት ነው።ስለዚህ የህይወት መጠቃት የስሜት ስቃይ ነው። በስሜት የያዝከው የበደል ምንጭ ነው። በደልን ለማስቆም ዋንኛው መንገድ የስሜትን ጥቃትን በይቅርታ መለወጥ ነው።
ህይወት የስሜት ትርጉም ብትሆንም ስሜት ሲጋነን የስሜት ስቃይ ነው። ህይወትን ለማጣፈጥ ስሜትን በብስለት አመዛዝኖ መኖር ነው። ለዚህ ደግሞ የሚሰማህን ሁሉ ከመኖር መኖር የሚገባህን በብስለት ማጥራት ነው። የስሜት ስቃይ በደል ከመሆኑ በፊት በበብስለት የሚጠራው በይቅርታ ነው። ማጥራት ካልቻልክ አንተን የሚበድለው የመጀመሪያው ሰው ራስህ ልትሆን ነው።
ብስለት በሴት ልጅ ላይ ውበት ሆኖ ራሱን ሲገልጥ ሁልም ነገር ከውጪ ወደ ውስጥ ነው። ስሜት በቁጣ አይወጣም። ፍቅር በጥላቻ ወደ ውጪ አይወጣም። የሴት ልጅ ብስለቷ ሁሉንም ስሜቷን በውስጧ አጣጥማ የምታስቀምጥበት ብቃት ነው። ይህ ብቃት ይቅርታ ራሱ ነው።
ሁልጊዜም ከበደለህ ሰው መጥፎ ድርጊት በላይ በጣም መጥፎ በደል የሰውየው ድርጊት ሳይሆን አንተ ስለድርጊቱ የሚሰማህ መጥፎ ስሜትን ማጥፋት አለመቻል ነው። ያለፈ በደልን በመጥፎ ገፅታው ደጋግሞ ማሰብ ራስን በራስ እንደመበደል ነው።
ይቅርታ ከማድረግህ በፊት አንድ ነገር አስብ። እሱም ወደፊት ተመሳሳይ ችግሮች ሊከሰቱ የሚችሉበት እድሎች ሰፊ መሆናቸውን መቀበል ነው።
ሰው የሆነ ጓደኛህ ሁሉ እንደሚወድህ እንጂ ወደፊት ምንም አይነት ስህተት ሊፈጥር እንደማይችል ቃል መግባት አይችልም። ምክንያቱም ስህተት የመኖር ውጤት በመሆኑ ምንም አይነት ስህተት አልሳሳትም በማለት ራሱን መግደል የሚፈልግ የለምና።
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment