አቅጣጫው የጠፋበት ትውልድ
በምእራባውያን አገራት ያለው ኢትዮጵያዊ ትውልድ የጉዞ አቅጣጫው የጠፋበት የማንነት ከርታታ ነው። በአንድ በኩል የሚኖርበት አገር ውስጥ ያለ ፈጣን ለውጥን እግር በእግር ተከትሎ ከፍጥነቱ ልክ መራመድ ያቃተው በሌላ በኩል ወደኋላ ጥሎት የሄደውን ማንነት የሚጎትተው ቢሆንም ወደዚህ ማንነት ለመመለስ የብቃት ችግር ውስጥ የሚገኝ ተቅበዝባዥ ትውልድ ነው።
ከሚኖርበት አገር ባህላዊና ሞራላዊ አስተሳሰብ ጋር ውህደት መፍጠር አቅቶት የምእራባውያኑ የህይወት ባቡር የተፋው፣ ስለመጣበት አገር ነባራዊ ሁኔታ ባለው አነስተኛ ግንዛቤ የመገለል ስሜትን እያዳበረ የመጣ፣ በራሱ ጊዜ ባይተዋር የሆነ ልቁሽቁሽ ትውልድ ነው።
የእነዚህ ትውልድ አባላት ነጮቹን በባለፈ ታሪክ "ኢትዮጵያ የረህበተኛ አገር ናት" ይላሉ ብለው ይወቅሷቸዋል። ይሁን እንጂ በወግ አጥባቂ ነጮቹ ዘንድ ኢትዮጵያን በሚመለከት ያለው የተንሸዋረረ አስተሳሰብ በነዚህ ኢትዮጵያዊ ነን በሚሉ ዲያስፖራ ትውልዶች ዘንድም የተተከለ ነው። እነዚህ በድሮ መረጃ ላይ ተመስረተው የአሁኗን ኢትዮጵያ የሚመዝኑ ምስኪን ዲያስፖራዎች አዲስቷ ኢትዮጵያን አሁንም ዜጎች የሚራቡባት፣ የሚገደሉባትና የሚጨቆንባት አድርገው ያስባሉ። አሁን በአገሪቱ የመጣውን የለውጥ ጭላንጭል ነጮቹ ቀድመው ሲቀበሉ እነዚህ የእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ለመቀበል አልቻሉም። በመሆኑም እነዚህ አካላት አንድም የሚኖሩበትን ማህበረሰብ መሆን ያልቻሉ በሌላ በኩል ደግሞ ጥለውት የመጡትን ማንነት ማደስ ያልቻሉ ቅብዝብዝ ትውልዶች በመሆናቸው የሚመለከተው አካል ትክክለኛውን አቅጣጫ በማሳየት ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል።
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment