ስነ ልቦና
ለማንኛውም ህይወት የሚሆን ሰብዕና ለመገንባት ሞክር። ህይወት የሚሊየን ክስተቶች ውጤት እንደሆነች እወቅ። የህይወትን ክስተቶች በአንድ ሰብዕና መጋፈጥ እንደማይቻል ተገንዘብ። የህይወትን የድምቀት ደረጃ ተከትሎ የሚተውን ሁለገብ የስነ ልቦና ይዘት ይኑርህ። ሲጨልም የሚያበራ፣ ሲደምቅ ከብርሀን የምትከላከልበት ሰብዕና ለመገንባት ሞክር።
መቆጣጠር የምትችለው ሰብእናህን እንጂ የህይወት ክስተቶችን እንዳልሆነ ተረዳ። ሲጨልም ለራስህ ብርሀን ሁን። ሲበራ ራስህን ከህይወት ጨረር ጠብቅ። በፍላጎትህና በምትችለው መካከል ያለውን ልዩነት ለማጣጣም የሚችል ሰብእና ይኑርህ። የምትፈልገውን ሁሉ መኖር አንደማትችል ተረዳ። መኖር የምትችለው የሚያስፈልግህን እንጂ የምትፈልገውን ሁሉ እንዳልሆነ አስብ። ሁሉ በአንተ እንዲኖር እንጂ ፣ አንተ በሁሉ ውስጥ ለመኖር አትሞክር። ሁሉ ወደ አንተ የሚመጣበትን መንገድ ይኑርህ። አንተ ወደ ሁሉ ለመሄድ አትሞክር። ሁሉ ለአንተ ተፈጠረ እንጂ አንተ ለሁሉ እንዳልተፈጠርክ እወቅ። የሚጠበቅብህን ህይወት ኑር አንጂ፣ የምትፈልገውን ሁሉ ለመሆን አትጠብቅ።
ለሁሉም ነገር መጠን አብጅ። ከፍታህን በቁመትህ ልክ አድርግ። ከራስህ በላይ የሆነ ከፈታ መፈጥፈጥ ሊያስከትል አንደሚችል አስብ። ውድቀትህም ከጫማህ በታች እንዳይሆን አድርግ። ከውድቀት በኋላ አልነሳም ብሎ ማሰብ ከጫማ በታች መቀበር እንደሆነ ገምት። ወድቆ መነሳትን ከቅርጫት ኳስ ተማር። ወድቆ የሚነጥር ማንነት ይኑርህ። ነጥሮም ቀለበቷ ውስጥ ነጥብ የሚያስቆጥር ህይወት ይኑርህ። ወደ ከፍታ የወጣ ሁሉ ስኬት እንዳልሆነ እወቅ። ውድቀት መቀበር እንደሆነ ሁሉ መነሳትም መንሳፈፍ እንዳይሆንብህ ጥንቃቄ አድርግ። በምትወድቅበት ጊዜ ላለመቀበር፣ በምትነሳበትም ጊዜ ላለመንሳፈፍ ይሆን።
ለማንኛውም ነገር ያለህ ስሜት የተመጠነ ይሁን። በጣምም አትዘን። በደስታም ብዛት አትስከር። በምትሳሳትበት ጊዜ የገነነ የጥፋተኝነት ስሜት አታዳብር። በስኬትም ጊዜ ከልክ ያለፈ ክብር አይሰማህ። ለራስህ የምትሰጠው ግምትና ለውጪው አለም ያለህ ስሜት ተመጣጣኝ አድርግ።
ህይወት ታማኝ እንዳልሆነች አስብ። ያለልክ ታማኝ ለመሆን እውነተኛ ነኝ በሚል አትመፃደቅ። ታማኝነት ለረጅም ጊዜ ተመሳሳይ የስሜት ተገዢ መሆን ሳይሆን አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ኃላፊነት የተሞላበት ማስመሰልንም እንደሚጨምር አስብ። ውሸት አልወድም አትበል። ውሸት በበጎ ጎኑ ተጠቀምበት። ውሸት አልወድም ማለት በራሱ ውሸት መሆኑን አስብ። ሁሉም የመሰለውን የሆነ እንጂ እስከአሁን ድረስ እውነትን የኖረ እንደሌለ ተረዳ። ሁልጊዜም ቢሆን እንቅስቃሴህን በሚያመጣው አወንታዊ ተፅዕኖ ለካ እንጂ ሂደቱ ላይ በመጨነቅ ጊዜ አታባክን። አንተ የምትመዘነው ሆነህ በተገኘኸው እንጂ ለመሆን ባልሆንከው ማንነት እንዳልሆነ እወቅ።
እጅግ በጣም ቁጥብ አትሁን። ከአስፈላጊ ተሳትፎ ይገድብሀልና። ቁጥብነት መልካም አጋጣሚ ልታገኝ የምትችልበትን መልካም አጋጣሚዎች እንደሚገድብብህ ተረዳ። ያለ ገደብም ነፃነትን አትመኝ። የተዝረከረከ ህይወት እንዲኖርህ ያደርግሀልና። ገደብ የሌለው ነፃነት መቆጣጠር ወደማትችለው ዝርክርክ ህይወት ውስጥ ሊያስገባህ እንደሚችል እወቅ። ህይወትህን የምትኖር ሁን እንጂ ህይወት አንተ ላይ እንድትኖርብህ አትፍቀድ።
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment