በኢትዮጵ ታሪክ መቻቻል ወይ?
በኢትዮጵያ ታሪክ መቻቻል ነበረ ወይ? ብዙ ሰው በተሳሳተ መንገድ ምላሽ የሰጠው ጥያቄ ነው። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው የሚለው ብሄል ከተረት ያለፈ ዋጋ የለውም። በተዝካር፣ በፅዋና መሰል ድግሶች አንድ ላይ መብላትና መጠጣት መቻቻልን ሊያመላክት አይችልም።
እንስሳትም በዚህ መልኩ በጋራ እየኖሩ በመሆኑ የሰው ልጅ በዚህ መልኩ መኖር ካልቻለ ሌላ ምን ሊጠበቅ ይችላል?? የአንድ ማህበረሰብ መቻቻል የሚለካው በተፋዘዘ አኗኗር ሂደት ውስጥ ባለው ድንዛዜ ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ልዩነቶች ውስጥ መኖር የሚያስችል ባህል ሲያዳብር ነው። ብዙም ልዩነት የሌለው አንድ አይነት ሊባል የሚችል አስተሳሰብና ባህል እያራማዱ በሚኖሩ ህዝቦች ውስጥ መቻቻል ሊለካ አይችልም። ዋናው ጥያቄ ኢትዮጵያውያኑ ከወግ፣ ባህላቸውና ከለመዱት አስተሳሰብ በተቃራኒ የሚገኝ አስተሳሰብ በመቻቻል አስተናግደው የመጡበት የመቻቻል ታሪክ አላቸው ወይ ነው መሆን ያለበት። የመቻቻል ብቃት በተመሳሳይ የአስተሳሰብ ማዕቀፍ ውስጥ በሚገኙ ጥቃቅን ልዩነቶች የሚለካ ሳይሆን ሰፊ የአስተሳሰብ ልዩነቶችን በብቃት በማስተናገድ የሚፈጠር የዳበረ ባህል ነው። መፋዘዝ መቻቻል አይደለም። መቻቻል ማለት ጊዜ የሚፈጥራቸውን ለውጦችን አጣጥሞ መኖር ነው። በሀይማኖት ታስሮ መኖር መቻቻል ሊባል አይቻልም። መቻቻል በተለያዩ ጊዜ የሚፈጠሩ ተቃራኒ አስተሳሰቦችን አጣጥሞ ማስተናገድ ነው።
በዚህ የተነሳ የኢትዮጵያ ታሪክ የብዝሀንነት ችግር ያለበት እንዲሆን አድርጓል። ብዙሀኑ ከሆነ የአስተሳሰብ ምንጭ የሚንቆረቆርለትን አስተሳሰብ ማዕቀፍ ውስጥ ተጠርንፎ ከመኖር ውጪ የተለያዩ አስተሳሰቦችን ያስተናገደበት ታሪካዊ ሂደት የለም። በአስርቱ ትዕዛዛት መመራት መቻቻል አይደለም። መቻቻል የሚባለው አስርቱ ትእዛዛት አስራ አምስት ይሁኑ ሲባል ልዩነቱን በብቃት ማስተናገድ ሲችል ነው። አንድ በሬ ከሱ በአፈጣጠር የሚለየውን በግ አልወጋውም ማለት ተቻችለው ኖሩ ማለትን አያመላክትም። በብዙሀን ተሳትፎ ያልተገነባ ታሪክን የመቻቻል ታሪክ ብሎ መውሰድ አስቸጋሪ ነው።

Comments
Post a Comment