ሚዛናዊ አስተሳሰብ
ሚዛናዊ አስተሳሰብ የሚዛናዊ ህይወት መሰረት እንደሆነ አስብ። የአንድ አስተሳሰብ እስረኛ አትሆን። የሰው ልጅ ብስለት የሚለካው አንድ አስተሳሰብ ላይ ሙጥኝ በማለት ሳይሆን የተለያዩ አስተሳሰቦችን በብቃት ማስተናገድ የሚችል አእምሮ በመገንባት እንደሆነ እወቅ።
አንድ አስተሳሰብ ብቻ ማስተናገድ ለህይወትህ ጠቃሚ የሆኑ ምቹ አጋጣሚዎችን መገደብ እንደሆነ ተረዳ። የአስተሳሰብ መብዛት የስኬት አማራጭ ማደራጀት እንደሆነ አስብ። ማንኛውም አስተሳሰብ ሀብት እንጂ ጠላት እንዳልሆነ አስታውስ። አስተሳሰብን መገደብ እውቀት የሚገኝበትን እድል መዝጋት እንደሆነ አስተውል። አንድ አስተሳሰብ በራሱ እስራት እንደሆነ ተገንዘብ። ብስልት ማለት የተለያዩ አስተሳሰቦችን በብቃት በማስተናገድ የሚገኝ የህሊና ነፃነት እንደሆነ አስብ። አንድ አስተሳሰብ ብቻ ማራመድ የህሊና ባርነት እንደሆነ ተገንዘብ።
የአንተ ህይወት እውነታ የሚወሰነው በገሀዱ አለም ባለው እውነታ ሳይሆን የአንተ እምሮ ገሀዱን እውነታ በሚረዳበት መንገድ እንደሚወሰን አስተውል። በህይወት መርህ መሰረት የህይወት እውነታ የአእምሮህ ስእል እንደሆነች እወቅ። የአእምሮህ የህይወት ስእል ጥራት ደግሞ ወደ አእምሮህ በምታስገባው የአስተሳሰብ አማራጮች እንደሚወን አስተውል። ብዙ አስተሳሰቦችን በመጠቀም የምትገነባው ህይወት ጠንካራና በቀላሉ የማይናድ እንደሚሆን አስብ። አንድ አስተሳሰብ ብቻውን ጨለማ የአስተሳሰብ አማራጭ ግን የህይወት ብርሀን እንደሆነ አስብ።
ህይወት ችግሯ ዘርፈ ብዙና እልፍ እንደሆነ ተገንዘብ። በህይወትህ የሚጋጥምህ ሁሉም ችግሮችን በአንድ መፍትሄ መቅረፍ እንደማትችል እወቅ። ለእያንዳንዱ ችግር የራሱ የሆነ መፍትሄ እንዳለው ተረዳ። ለብዙ ችግር አንድ አስተሳሰብ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል አስተውል። ከሚያጋጥምህ ችግር ባህሪ ጋር የሚመጣጠን መፍትሄ ይኑርህ። ለብዙ ችግሮች ብዙ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ ተረዳ። ብዙ መፍትሄ ለማግኘት ደግሞ ብዙ አስተሳሰቦች በብቃት ለማስተናገድ ዝግጁ ከመሆን እንደሚጀምር አስተውል። ብዙ አስተሳሰቦችን ማስተናገድ የዳበረ አእምሮ ለመገንባት የሚረዳ የአእምሮ ጂምናስቲክ እንደሆነ እወቅ። ብስለት የሚለካው ብዙ አስተሳሰቦችን በማብላላት በሚገኝ የማሰብ ብቃት እንደሆነ ተረዳ። ሰውነትህ እንዲዳብር የተለያዩ የተመጠጣኑ የምግብ አይነቶች እንደሚያስፈልጉ ሁሉ ለአእምሮህ መዳበርም የብዙ አስተሳሰቦች መመጣጠን ወሳኝ እንደሆነ አስብ።
ለሁሉም የህይወት አይነት የሚሆን ጠንካራ ስነ ልቦና የብዙ አስተሳሰቦች ውጤት እንደሆነ አስብ። የሰው ልጅ ስነ ልቦና የስሜት ክምችት እንደሆነ አስብ። ጥራት ያለው ስሜት የሚፈጠረው ደግሞ ጥራት ያላቸውን አስተሳሰቦችን በማደራጀት እንደሆነ ተገንዘብ። የብዙ አስተሳሰቦች አማራጭ ጥራት ያላቸው ስሜቶችን እንደሚፈጥር፣ ጥራት ያላቸው ስሜቶችም ስነ ልቦናን እንደሚገነባ አስተውል። ደካማ የተሸናፊነት ስሜት የአስተሳሰብ አማራጭ እጥረት መሆኑን ተገንዘብ። ከደም ማነስ በከፋ መልኩ የአስተሳሰብ ማነስ ራስ የሚያዞር ችግር መሆኑን ተረዳ። የተለያዩ አስተሳሰቦች የአእምሮ ምግብ እንደሆነ ተገንዘብ። አእምሮህን አታስርብ። በሚመጥነው መልኩ የሚችለውን ያህል አስተሳሰብ በየጊዜው ካልመገብከው በረሀብ መንምኖ እንደሚቀጥን አስብ። አእምሮህ እንዲቀጥን አታድርግ። ከሰውነትህ የቀጠነ ባዶ አእምሮ የህይወት ሸክም እንደሆነ አስብ።
አስተሳሰብ ስታራምድ በሁለት ጫፍ ላይ አትገኝ። ትክክለኛ እውነት በየትኛው ጫፍ እንደሆነች ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም። በአስተሳሰብ ጫፍ ላይ መገኘት ከእውነት የሚኖርህን ርቀት እንደሚጨምር ተረዳ። መሀል ላይ መሆን ለእውነት የሚኖርህን ርቀት በግማሽ መቀነስ የሚያስችል መሆኑ ጫፍ ከመሆን ይልቅ መሀል ላይ መገኘት ወደ እውነት ለመድረስ የመቅረብ እድል እንደሚያሰፋ ተረዳ።
እምነትን ለመከላከል ስትል ከአዳዲስ አስተሳሰቦች አትቆጠብ። የብዙ አስተሳሰብ መኖር የግል እምነትን ለማጠናከር እንደሚረዳ እመን። እምነትህንና የምትቀበለውን አስተሳሰብ በብቃት ማስተናገድ ብስለት መሆኑን ተረዳ። በባዶ የተገነባ እምነት ጅልነት እንደሆነ እወቅ። አእምሮህን የአንድ አይነት አስተሳሰብ ብቻ ማጠራቀሚያ በርሜል አታድርግ። በሚያስፈልግ ጊዜ የሚያፈስ፣ ሲያስፈልግ የሚቀዳ አእምሮ ይኑርህ። በፍየል ዘመን በግ አትሁን። በማንኛውም ጉዳይ ላይ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል አስብ። አንድ አስተሳሰብ ብቻ ነክሰህ ድርቅ አአትበል። የነክሶ መድረቅን ችግር ከጉንዳን ተረዳ። ነክሶ ድርቅ ያለ ጉንዳን የነከሰውን ካለቀቀ በሚጎተትበት ጊዜ አንገቱ እንደሚቆረጥ አስብ። ቀጭን አንገት ይዘህ ወፍራም ድርቀት አይኑርህ። ስትጎተት ትቀነጠሳለህና!
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment