ግልፅነት ለጓደኝነት
በጓደኝነት ውስጥ ግልፀነት አስፈላጊ ነው። አንተ ግልፅ ሆነህ የቀረብከው ጓደኛ፣ ከአንተ የሚደብቀው ነገር ከበዛ ፣ ጓደኝነቱን ሲጨርስ ጠላት ለመሆን አስቀድሞ እያመቻቸ ነው።
እሱ በሚሰማው መልኩ ጓደኛ እንድትሆን የሚፈልግን ሰው አንተ የሚሰማህን እንዲሰማው ማድረግ የምትችለው እንዲሰማው የማይፈልገውን እንዲሰማው ማድረግ ስትችል ነው።
በጓደኝነት ውስጥ ታማኝነት የሚለካው በቃል የተናገሩትን በተግባር ለመተርጎም በሚደረግ ጥረት ነው። ይህ ካልሆነ ግን በተግባር መተርጎም የማትችለውን ነገር በቃል አለመናገር በራሱ ታማኝነት ነው።
ጓደኛህ ስትፈልገው መቅረብ ካልቻለ ፣ ሳትፈልገው መራቅ ካልቻልክ የሚኖርህ አማራጭ በፈለገህ ጊዜ ቀርበኸው ፣ ባልፈለከው ጊዜ ማራቅ ነው።
በጓደኝነት ውስጥ በደስታ ጊዜ አንድ ላይ እንደመጫወት የመሰለ ጣፋጭ ነገር ፣ በችግር ጊዜ ለብቻ መጣላትን የመሰለ መራራ ነገር የለም። በደስታ ጊዜ አብሮህ የተደሰተ ጓደኛ ፣ በችግር ጊዜ አብሮ ሆኖ ካልተጣላህ ፣ መጀመሪያም ከአንተ የሚፈልገው ጓደኝነት ሳይሆን የራሱን የህሊና ምቾት ነው። በደስታ ጊዜ አብሮህ ሆኖ ተጣልቶ የማይለይህ ከጓደኝነታችሁ በላይ ራሱን ጓደኛ ያረገ ነው።
ጓደኞችህ እንደሚወዱህ ቢነግሩህም መውዳዳቸው ትክክል የሚሆነው አንተን እንደወደዱህ እንዲሰማህ ማድረግ ሲችሉ ነው።እንወድሀለን በሚሉት ደረጃ መውደዳቸው ካልተሰማህ በአካልህ በጓደኞችህ መሀል ብትሆንም በስሜትህ ግን ብቸኛ ነህ።
የጓደኛህ ችግር መረዳት ያለብህ ጓደኛህም የአንተን ችግር መረዳት ከቻለ ነው። የአንተን ችግር መረዳት ያልቻለን ጓደኛ ፣ ችግሩን ለመረዳት የምትገደድ አለመሆኑ በራሱ ሊረዳልህ የሚገባ ችግር ነው።
የአንተን ስሜት ሳይጠብቅ የእሱን ብቻ ስሜት እንድትጠብቅለት የሚፈልግ ጓደኛ፣ የአንተን ስሜት እንዲጠብቅ የምታደርገው የእሱን ስሜት በማጥቃት ብቻ ነው። እሱ ከሚሰማው ስሜት ውጪ ፣ አንተ የሚሰማህ ካልተሰማው፣ ስሜቱን አለመጋራትህን እንዲሰማው አድርገው።
ሳትፈልገው ቀርቦህ ስትፈልገው የሚርቅህን ሰው ጋር ማድረግ ያለብህ ነገር በራቀህ ጊዜ እሱን አለመፈለግን ማስለመድ ነው። በዛው ይንካው!
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment