ሰው መሆን

ሰው መሆን በስጋ ሳይሆን በአስተሳሰብ ነው። ሰው አስተሳሰቡ እየዳበረ ካልሄደ ደም የሚንሸራሸርበት ድንጋይ ነው። ትንሽ ከፍ ካደረግነው  ማሰብ እየቻለ ካላሰበ ሰውም ከብት ነው። የሰው ልጅ ጊዜው ከሚጠይቀው ለውጥ ጋር የሚመጣጠን አስተሳሰብ ይዞ መገኘት ካልቻለ፣ የሚኖርበትን ቦታ ለህልውናው ምቹ ማድረግ የሚያስችል የአስተሳሰብ ምንጭ መሆን ካልቻለ ከከብት በምን ተሻለ?



በዚህ ትርጉም መሰረት ወደ ፊት በመሄድ ሰው መሆን ሲገባቸው ወደኃላ ተስበው ከበት የሆኑ ህዝቦች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ኢትዮጵያኑ ስጋቸው በሚጠይቃቸው ደረጃ አእምሯቸው ማሰብ አልቻለም። ትልቅ ስጋ ተሸክሞ ትንሽ ማሰብ በሬ መሆን ማለት ነው። የሰው ልጅ በሬን የመጥመድ መብት እንዳለው ሁሉ መንግስትም ኢትዮጵያውያን ለማልማት ዜጋውን ጠምዶ የማሰራት መብት አለው። መብቱ ፖለቲካዊ ሳይሆን ከተፈጥሮ ህግ የሚመነጭ ነው።

ኢትዮጵያውያን ለፕላኔታችን አልመጠኗትም። ጥገኛ ሆነዋል። ኢትዮጵያን የአገራቸውን መሬት ከውጪ ወራራ በመጠበቅ ፣ ራሳቸውም እንዳያለሟት እርስ በርስ በመጠባበቅ ኖረዋል። እግዜአብሔር ለሌሎች ህዝቦች መሬትን ኑርባት ሲለው፣ ለኢትዮጵያን ደግሞ መሬትን ጠብቃት አለው። ይኼው እስከአሁን ድረስ መሬታቸውን ሳያለሙ እየጠበቁት ነው። አደራ ጠባቂ ህዝብ!

ኢትዮጰውያን ውጪ አገር ሲሄዱም የሚኖሩበት አገር ጥገኛ ናቸው። በሰው አገር እንደባሪያ ሆነው የሚኖሩትም ከጥገኛ ማንነታቸው ነው። ኢትዮጵያውያን ውጪ አገር ሲሄዱ እንደ ግለሰብ የናሳ ተመራማሪ ይሆኑና እንደ ማህበረሰብበ አገር ቤት ያለው መንግስት ተቃዋሚ ይሆናሉ። እንደግለሰብም እንደማህበረሰብም የሚሰሩት ነገር አንድም የማይፈለግ ነገር ፣ ሁለትም የሚፈለገውን በማበላሸት ነው። ቻይና ድልድይና ረጅም መንገድ ሲሰራ ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ቤተ ክርስቲያንና መስኪድ ይሰራሉ። ከህንድ የሄዶት ለአገራቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር ፈጥረው ስፔስ ላይ ሲወጡ ኢትዮጵያኑ ደግሞ ባሉበት ሆነው ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ።

በምእራባውያን አገራት የሚኖሩ የሌላ አገር ተወላጆች እንደኢትዮጵያኑ ሁሉ እርስ በእርስ ይከፋፈላሉ። ልዩቱ ግን የክፍፍሉ ምንጭ ነው። ህንዳዊ ዲያስፓራ እርስ በእርሱ የሚከፋፈለው ውድድርን መሰረት በማድረግ ነው። በዚህ መሰረት ህንዳዊ ማህበረሰብ ሲከፋፈል ሚድል ክላስ፣ ሀየር ክላስ፣ ፕሮፌሰር፣ ዶክተር ብሎ ነው። ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች የሚከፋፈሉበት መሰረት ደግሞ በመተዛዘል ነው። ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራ። ከዚህ አለፍ ካለ ሊከፋፈል የሚችለው አገር ቤት መጥቶ በቀመጨለው ቺክ ብዛት ነው።

ድሮ በኢትዮጰያውያን ማህበረሰብ ውስጥ ጀግንነት የሚለካው አገር ሳይለቅ የገዛ ምድሩ ላይ ሞትን በመጋፈጥ ነው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው አፄ ቴዎድሮስ ጀግና በተባሉበት ጀግንነት ተመዝነው አፄ ኃ/ስላሴ በባእድ ወረራ ጊዜ ሱዳን በመሄዳቸው ጀግንነት ተቀነሰባቸው። አሁን ያ ጊዜ አልፏል። አሁን ላይ በኢትዮጵያውያን ጀግንነት የሚባለው ወደ ውጪ አገር ተሰዶ በቴሌቪዥን በመታየት ነው። ወይ ደግሞ ጎረቤት አገር ሆኖ አድፍጦ በመታየት ነው። ድሮ የቀረው ይኼ ነው።

ወደ ውጪ አገር በሄድክበት ብዙ ኢትዮጵያውያን ያሉበት ቦታ ራስህን ካገኘህ ቦታ ቀይር። ምክንያቱም ከኢትዮጵያኑ ጋር ከቆየህ አገር መቀየርህም ራሱ ያስቀይሩሀል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የከተማ አወቃቀር የሰለነጠነ አይደለም። የሰለጠነ የከተማ ዲዛይን የለውም።ከተማው ለከተማ መሰረተ ልማት አይመችም። ኢትዮጵያዊ የከተመው ከተማ ለመባል ያልሰለጠነ ከተማ ነው። በዚህ የተነሳ ከተማው የሚመስለው የሰው ልጅ መኖሪያ ሳይሆን የከብቶች በረት ነው።ይህን ተከትሎ የሚነሳው ድምዳሜ ሁለት ነው። የኢትዮጵያኑ  ከተማ የተመሰረተው አንድም በከበት ነው። ወይ ደግሞ ከተማውን የመሰረቱት ኢትዮጵያውያን ከብት ተከትለው ነው። ዞሮ ዞሮ ከብት የሰራው ከተማ ነው። ለውጡም የተደናቀፈው በከብት ነው።

አገሬን እወዳለሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ብዙ ነው። ከሙሁሩ እስከ ዘፋኙ፣ ከፖለቲከኛው እስከ አትክልተኛው ሁሉም አገሩን የሚወድ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነው። አገሩን የሚወደው ግን ውጪ ሆኖ ነው። አገር ቤት የሚጠላዉ ነገር ብዙ ነው። አምባገነን መንግስት፣ ያልበሰለ ሹሮ፣ ቆሻሻ ውሀ፣ የኔትወርክ መቋረጥ ፣ እርዳን የሚሉትን ቤተሰቦችና የቀድሞ ጓደኞች ወዘተ። ሁሉንም አይወዳቸውም። አገር ቤት የሚጠላው ነገር በዝቶ ፣ ውጪ ሲሄድ የሚወደው አገሩን ሳይሆን የአገሩን ካርታ ነው።

አንድ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ሲሆን ሁለት ነገር ያደርጋል። በመጀመሪያ በአገራዊ ግንባታ ሂደት ራሱን ያገላል። ሁለተኛ የራሱን ተሳትፎ ባሸሸበት ጉዳይ ላይ የሰራው አካል ሲሳሳት ስህተት ለመልቀም ይመለሳል።

ኢትዮጵያውያንና ይቺ ፕላኔት አሁንም ድረስ አልተስማሙም። ኢትዮጵያውያኑ ለመኖር የሚፈልጉት ፣ በራሳቸው ተሳትፎ ሳይሆን የሌሎች ድክመት በሚፈጥረው ትራፊ ህይወት ነው።

ኢትዮጵያውያን አንድም ጊዜ አንድ መሆን ያልቻሉ የተለያዩ ህዝቦች ናቸው። ኢትዮጵያኑ በልዩነታቸው መሀል አንድ ሆነው ካገኘሀቸው በሁለት ምክንያት ነው። በልዩነታቸው አንድ ሆነው ያየሀቸው ወይ ፎቷቸውን ነው። ወይ ደግሞ ልዩነታቸውን ለመረዳት የሚያስችል ብቃት በጎደላቸው ሰአት ነው። የመጀመሪያው ተስለው ነው። ሁለተኛው ላይ ተፈዛው ነው።

Posted by EthioSophi Admin

Comments

Popular posts from this blog

የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?

የማካቬሌ ፍልስፍና

የፍቅር ትርጉሙ