ልማት የማን ነው?
በመርህ ደረጃ ልማት የህዝብ መብት ነው። ለመንግስት ደግሞ ግዴታ ነው። ነገር ግን ልማት የህዝብ መብት ነው ሲባል ህዝብ ልማት የመጠየቅ መብት አለው ማለት እንጂ በግልባጩ ልማት አልፈልግም የማለት መብት አለው ማለት አይደለም። ይህ አይነት የህዝብ ዝንባሌ ከተፈጠረ ልማት የማስፈን ጉዳይ የመንግስት መብት ይሆናል። መንግስት ማለት መንግስታዊ ስርአቱ በመሆኑ የልማትን ጉዳይ የመወሰን መብት የስርአቱ መብት ይሆናል።
ህዝብ የሚፈልገውን የልማት ጥያቄ ማንፀባረቅ እንጂ ከስርአቱ ልማት አልፈልግም የማለት መብት የለውም። ለምን? የመጀመሪያው ጉዳይ የህዝቡ መብት በስርአቱ የሉአላዊነት ጥላ ስር የሚታይ መሆኑ ነው። ህዝቡ የውሳኔ መብቱን ለስርአቱ በመስጠት የተስማማ በመሆኑ የህዝቡ መብት በስርአቱ ስር የሚታይ ነው። ስለዚህ የስርአቱን ፍላጎት የሚጥስ ሆኖ ከተገኘ የህዝብ መብት ሊሆን አይችልም። ሁለተኛው ጉዳይ ልማት የመንግስት ግዴታ ከመሆኑ አንፃር ሊታይ የሚችል መሆኑ ነው። በስርአቱ ውስጥ የመንግስት አስፈላጊነት አስገዳጅ የሆነበት ምክንያት ልማት በመንግስት ሚና ተፈፃሚ የሚሆን ፖለቲካዊ ተልእኮ በመሆኑ ነው። ህዝብ ልማት አልፈልግም የማለት መብት አለው ማለት መንግስት ልማት የማምጣት ግዴታውን ተግባራዊ የማድረግ መብቱን የሚፃረር ነው ማለት ነው። ዜጎች መንግስት የማይነካባቸው የራሳቸው መብት እንዳላቸው ሁሉ መንግስትም ዜጎች ሊነኩበት የማይችሉት ግዴታን የመወጣት መብት አለው። ይህ የመንግስት መበት ሉአላዊነት ይባላል። በዚህ መሰረት መንግስት ልማት የማልማት ግዴታውን ተግባራዊ የማድረግ መብቱን ማንም አካል ሊነካበት አይችልም።
Posted by EthioSophi Admin

Comments
Post a Comment