በቬገንስታይን እይታ: ፍልስፍና ምንድነው?

"ፍልስፍና ምንድነው?" የሚለው ጥያቄ በርካታ ፈላስፋዎችን በልዩነት ያፈላሰፈ ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ ሁሉም ፈላስፋዎች በፍልስፍና ባህሪ ላይ የሰጡት ትርጉም ሰፊ ልዩነት ያለው ነው። ለምሳሌ:

ለሶቅራጥስ ፍልስፍና የነፍስ ማንነትን ለመኖር ስጋን መግደል ማለት ነው። በሶቅራጥስ ሌላ ትርጉም አለማወቅን ማወቅ ፍልስፍና ነው።

image

የፕሌቶ ፍልስፍና ትርጉም ከስሜት ደረጃ የዘለለ የነፍስ እውነታ ለመረዳት የሚያስችል የሁለተኛ ደረጃ  ግንዛቤ ነው። ለአርስቶትል ፍልስፍና የሁሉም ጥናቶች አባት የሆነ  ጥቅል ሳይንስ ነው። በሌላኛው ትርጉሙ አርስቶትል ፍልስፍናን ሲገልፀው የመገረም ወይም የመደነቅ ስሜት የሚፈጥረው የማወቅ ጉጉት ማለት ነው። ፍልስፍና ለካርል ማርክስ የለውጥ ሂደት ነው። በአጠቃላይ በፍስፍና ባህሪ ላይ የተሰጡት ትርጉሞች በስፋትም በልዩነትም ሊታዩ የሚችሉ ቢሆንም በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል ። አንደኛው የትርጉም አማራጭ  ፍልስፍናን በራሱ እውቅት አድርጎ የሚወሰድ ሲሆን ሁለተኛው ትርጉም አማራጭ ፍልስፍናን እውቀት ሳይሆን የእውቀት መንገድ አድርጎ የሚወሰድው ነው። የመጀመሪያው የትርጉም አማራጭ በማንኛውም ጉዳይ ላይ በማንኛውም መልኩ የሚፈጠር አስተሳሰብ በራሱ ፍልስፍና አስርጎ የሚወሰድ ነው። ይህ ትርጉም አጠቃላይ የአለማትን እውነት አሳብና ስሜት አዋቅሮ  በማንኛውም የአስተሳሰብ ቅርፅ መፍጠርን መሰረት የሚያደርግ ስነ ኑባራያዊ ውክልና (Metaphysical make up) ግንባታ ላይ የሚያተኩር ነው። ለምሳሌ ፣ መሬት ክብ ናት ወይም መሬት ጠፍጣፋ ናት የሚለው የመሬትን እውነታ በአስተሳሰብ የመወከል ጉዳይ በመሆኑ ይህ በራሱ ፍልስፍና እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በሁለተኛው የትርጉም አማራጭ ፍልስፍና በራሱ አስተሳሰብ ሳይሆን አስተሳሰብ የመፍጠር ሂደት ነው። በዚህ መሰረት መሬት ክብ ናት የሚለው አሳብ በራሱ አስተሳሰብ ሳይሆን የማሰብ ሂደት ነው። በዚህ መልኩ የሚወሰደው የፍልስፍና ትርጉም ፍልስፍና ማለት ማወቅ ሳይሆን የማወቅ ሂደት፣ አስተሳሰብ ሳይሆን የማሰብ ሂደት፣ ጥበብ ሳይሆን የጥበብ መንገድ እና የመሳሰሉትን የመጠየቅና ምላሽ የመፈለግ፣ የመጠራጠር ወዘተ ሂደቶችን የሚያመላክት እንደሆነ ሊወሰድ ይችላል።  የቨገንስታየን የፍልስፍና ትርጓሜ ከሁለተኛው ሊመደብ የሚችል ነው።

image

የቬገንስታይን የበኩር ስራ በሆነው Tractus Logico -Philosophics የተሰኘች መፅሀፍ የፈላስፋው ቀዳሚ ስራ ስትሆን በዚች አጭር ስራዉ ቬገንስተን ዘለግ ያለ እድሜ ባስቆጠረው የምራባውያኑ ባህል ስሙን መትከል ችሏል። በመፅሀፏ ቬገንስታዬን ስለ አለም መሆን፣ ሀቅ፣ የፍልስፍናን ባህሪ እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ከሎጂክ አንፃር ለመቃኘት ሞክሯል። ቬገንስታይን በዚህ ስራው ላይ የፍልስፍና ትርጉም ምን ሊሆን እንደሚገባ ያለውን እይታ አስፍሯል። የፈላስፋው የፍልስፍና ትርጉም ፍልስፍናን ራሱን ችሎ እውቀት ተደርጎ የሚወሰድ ሳይሆን የእውቀት መንገድ በሚለው የአሳብ ትንታኔ የሚወሰድ ነው። ፍልስፍና በተለምዶ ያለው ትርጉም አንድም ፍልስፍና በራሱ እንደእውቀት በሌላ መልኩ ፍልስፍና የሳይንስ ዘርፍ ተደርጎ ይወሰዳል። ቬገንስታይን በፍልስፍና ትርጉሙ ፍልስፍና የሳይንስ ዘርፍ ሳይሆን የሳይንስ የጥናት መንገድ ነው በሚል ያስቀምጣል። ፍልስፍና የዝርዝር ጉዳዮች ይዘት ሳይሆን ወደ የተሻለ አሳብ የሚያመራ የአሳብ ማጥሪያ መንገድ ነው።በዚህ እይታ ከተወሰደ አንድ ሰው ፈላስፋ  ነው ማለት እውቀት ያለው ማለት ሳይሆን ወደ እውቀት የሚያመራ የእውቀት  ጥናት ላይ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል።

ፍልስፍና የአሳብ ማጥሪያ መንገድ አንጂ የአሳብ ክምችት አይደለም። ስለዚህ ይላል ቬግንስታይን " ፈላስፋዎች ማድረግ ያለባቸው ንድፈ አሳቦችን ማበራከት ሳይሆን ጥርት ወደአለው ትክክለኛ አሳብ መሄድ ነው" ከፍልስፍና የሚገኙት በርካታ ንድፈ አሳቦች መኖራቸው ትክክለኛ የፍልስፍና ትርጉምን አያመላክትም። ትክክለኛ የሆነ የተሻለ አሳብ የሚገኘው ከዚህ በፊት የተገኙትን ንድፈ አሳቦች ላይ ተጨማሪ አሳቦችን መጨመሩ ብዥታ የሚፈጠርበትን እድል ማበራከት ነው። በመሆኑም ፍልስፍናን እንደ አስተሳሰብ መውሰዱ ትክክል አይደለም። የፍልስፍና ትርጉም የተሟላ የሚሆነው ፍልስፍና የአሳብ ማጥሪያ መንገድ ሆኖ ሲታይ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው የፍልስፍና ትርጉም አስፈላጊ አይሆንም -- እንደቬገንሰታይን እምነት።

Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?

የማካቬሌ ፍልስፍና

የፍቅር ትርጉሙ