የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?
በፍልስፍና ፍቅር ሊታይ የሚችልበትን ትንታኔ በሁለት መልኩ ከፍሎ ማየት ይቻላል። የመጀመሪያው ፍቅርን ከህልውና ጋር በማያያዝ "ፍቅር በገሀዱ አለም አለ ወይስ የለም?" የሚለው አሳብ ሲሆን ፍቅርን ዛፍ፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ እና የመሳሰሉት ቁሶች በራሱ ህልውና አለው ወይ? ካለው የህልውናው መገለጫ
ምንድነው? ወዘተ የሚሉትን የስነ ኑባሬ ጥያቄዎች መነሻ አድርጎ የሚታይበት የነባራዊነት ትንታኔ ነው።
ሁለተኛው የፍቅር ትንታኔ ከስነ ልቦና፣ ሞራልና ፖለቲካዊ ጉዳዮች አንፃር ለማየት የሚኬድበት መንገድ ሲሆን የመጀመሪያውን እይታ ለሌላ ጊዜ በማቆየት በሁለተኛው መንገድ በፍልስፍና ፍቅር የሚተነተንበትን መንገድ ለማስረዳት እሞክራለሁ።
በዚህ መልኩ ፍቅር ሊታይ የሚችልባቸው የተለያዩ አሳቦች አሉ። የመጀመሪያው ፍቅር ከመሆን ማንነት ጋር የሚያያዝበት ገፅታው ነው። ለምሳሌ፣ እኔ ፈላስፋ መሆን እወዳለሁ በሚለው አገላለፅ ወስጥ "ፍቅር ፈላስፋ በመሆን" የሚገለጥ የማንነት ፍቅር ይሆናል። በዚህ መሰረት የህግ ጠበቃ፣ አስተማሪ፣ ባል፣ ሚስት የማሳሰሉትን የሞራል ማንነትቶችን ለመሆን ወይም በመሆን የሚገለፅ ፍቅር ነው። ሁለተኛው የፍቅር አሳብ "በመሳተፍ" የሚገለፅበት የፍቅር ገፅታ ነው። ለምሳሌ:" እኔ እግር ኳስ መጫወት እወዳለሁ" በሚለው አገላለፅ "ፍቅር እግር ኳስ በመጫወት" የሚገለጥ የተሳትፎ ፍቅር ነው። በሶስተኛ ደረጃ ፍቅር ከእሴት አንፃር የሚወሰድበት አግባብ ነው። ለምሳሌ: "እኔ ጨዋ ልጅ እወዳለሁ" ማለት እኔ ጥሩ እሴት አድርጌ የምወደውን እሴት ያላት "ጨዋ" ሴት እወዳለሁ ማለት ነው። እዚህ ላይ የፍቅር መገለጫው "ልጅ" የሚለው ሳይሆን "ጨዋ" የሚለው እሴት ይሆናል።

በሌላ መልኩ የፍቅር ትርጉም የሚታይባቸው ሶስት እይታዎች አሉ። እነሱም: ሀ) ፍቅር ህብረት ነው ። ለ) ፍቅር የይገባኛል ውሳኔ ነው። እና ሐ) ፍቅር እሴት ነው የሚሉት ናቸው።
የመጀመሪያው አሳብ " ፍቅር ህብረት ነው" የሚለው ነው። በዚህ አሳብ መሰረት ፍቅር "እኔ" የሚለውን "እኛ" ወደ ሚል የጋራ ማንነት ያለው ህብረት የሚፈጠርበት ነው። የሰው ልጅ የተናጠል ማንነት ያለው ነው። አንተ፣ አንቺ፣ እኔ፣ እሱ፣ እሷ የሚሉት የተናጠል ማንነቶች የጋራ ማንነት የሚፈጥሩት በፍቅር በመሆኑ ፍቅር ህብረት ነው። የሰው ልጅ በተናጠል ሲኖር ለራሱ ካለው ፍቅር የሚመነጭ የራሱ የፍላጎት ስሜት አለው። በግል ያለው የተናጠል የፍላጎት ስሜትን ከሌላው አቻ ስሜት ጋር በማጎዳኘት የስሜት ውህደት የሚፈጠርበትና አንድና ከዛ በላይ የሆኑ የተለያዩ ፍላጎቶች የሚዋሀዱበት መንገድ ፍቅር ነው። ቤተሰብና ማህበረሰብ የተፈጠረው በፍቅር ህብረት የተለያዩ የተናጠል ፍላጎቶችን በጋራ ፍላጎት ስር በማድረግ በሚፈጠር ህብረት ነው። ስለዚህ ፍቅር ማለት የስሜት ውህደት የሚደረግበት ህብረት ነው።
በሌላ መልኩ ፍቅር የህብረት ጉዳይ ሳይሆን ሐ) ፍቅር የይገባኛል ውሳኔ ነው የሚለው አሳብ ነው። ፍቅር ስሜትም እውቀትም አይደለም።ፍቅር ማለት ህብረት መፍጠር ሳይሆን ራስ ጋር የሌለን ገዳይ የመጋራት ፍላጎት ነው። ፍቅር ማለት አንድን ጉዳይ ለራስ ካለው የተለዬ ጥቅም አንፃር የመወሰን የይገባኛል ሂደት ነው። አበበ ቤተልሔምን አፈቀረ ማለት አበበ እሱ ጋር የሌለና ቤቴልሔም ጋር ያለ ጥቅም ተካፋይ ለመሆን የሚወስነው ውሳኔ ነው። የሰው ልጅ ህብረት ለመፍጠር ከምድር ተነስቶ ጓደኛ ወይም ህብረት አይፈጥርም። ቢያንስ ወደ ህብረቱ ለመቀላቀል ውሳኔ የሚያበቃው የቁስ ወይም የስነ ልቦና ጥቅምን መሰረት ያደርጋል። በዚህ መሰረት ፍቅር ማለት ህብረት ሳይሆን በአንድ ነገር ላይ የሚፈጠር የይገባኛል ስሜት ተነሳስቶ የሚፈጠር የጥቅም መጋራት ፍላጎት የሚፈጥረው ውሳኔ ነው።
በሶስተኛ ደረጃ የፍቅር ትርጉም የሚታይበት መንገድ ሐ) ፍቅር በራሱ እሴት እንደሆነ አድርጎ የሚመለከተው አሳብ ሲሆን ይህን አሳብ በሁለት መልኩ ማየት ይቻላል።ሁለቱን አሳቦች ለመረዳት የሚከተሉትን ምሳሌ አገላለፅ ለመረዳት ሞክር። ሀ) አስቴር መፈቀር ስላለባት አበበ አስቴርን ያፈቅራታል። ለ) አስቴር አበበን ስላምታፈቅረው አበበም ያፈቅራታል። በመጀመሪያው ምሳሌ (ሀ) አበበ አስቴርን የሚያፈቅራት ከምንም ተነስቶ ፍቅርን በራሱ ዋጋ ሰጥቶ ነው። ለአበበ አስቴርን የሚያፈቅራት ማፍቀር በራሱ ትክክለኛ ዋጋ ያለው ስለሆነ ነው። ስለዚህ አስቴር ትወደደውም ትጥላው አበበ ለፍቅር ባለው ዋጋ የተነሳ አስቴርን ይወዳታል። ይህ አሳብ ፍቅር ለመፈቀር ሳይሆን ፍቅር ለፍቅር እንደማለት ነው። ስለዚህ በዚህ የፍቅር አይነት መነሻው ፍቅር በራሱ ትክክል እንደሆነ የማፅደቅ ጉዳይ ነው። በሁለተኛው ምሳሌ (ለ) አበበ አስቴርን የሚያፈቅራት አስቴር ስለምታፈቅረው ነው። የፍቅሩ መነሻ ለፍቅር ዋጋ በመስጠት ሳይሆን ከሌላ ሰው የሚሰጠውን የፍቅር ምላሽ መነሻ በማድረግ ነው። በዚህ መልኩ የሚኖረው ፍቅር አፍቃሪም ተፈቃሪም መነሻቸው የሚሰጣጡት ፍቅር ይሆናል ።
.... ይቀጥላል!

well waiting for the next....article!..
ReplyDeletewaiting for the next article!....its enjoyable and too helping to good consciousnes!
ReplyDeleteጎበዝ በርታ የበለጡ ብዙ ጽሁፎችን እጠብቃለው ካንተ
ReplyDeletegreat view keep it up man
ReplyDeleteLiyu new wadijewalew hasabun
ReplyDeleteGambling and Online Gambling - DrMCD
ReplyDeleteIn the 1990s, the United 의왕 출장마사지 States came into a mature world 경주 출장샵 of gambling. It's been growing in popularity 안동 출장샵 as a result 서귀포 출장샵 of increased activity from online 여수 출장마사지 gambling