Posts

ጠቃሚ ምክር

ሌሎች እንዴት ማጥቃት እንዳለብህ የሚነግርህን ሰው  ሌላ ጊዜ እሱ ሲያጠቃህ እንዴት መካለከል እንዳለብህ እየነገረህ እንደሆነ ተረዳው። ሌሎችን ቀርበህ እንዴት እንደምትወድ የሚነግርህን ሰው ግን ለፍቅር እድል ስጠው። ሰውን ማመን ቀብሮ ነው የሚለው አስተሳሰብ  ስህተት ነው። ለማመን ሰው መቅበር ካስፈለገ የተቀበረን ለማመንም መቀበር ሊያስፈልግ ነው። ሰውን የማምነው ቀብሬ ከሆነ ሌሎችም እኔን የሚያምኑኝ ቀብረውኝ ነው። መኖር ግዴታ በሆነበት ህይወት ውስጥ ሞት መብት አይሆንም። ማንኛውም ሰው ራሱን በህይወት ማቆየት እንጂ ለመሞት ራሱን መግደል አይችልም። ነገር ግን ራስን ለመግደል ቀላል ዘዴ አለ። መጀመሪያ ማሳብ ማቆም። ቀጥሎ ማሰብ ያቆምከውን አሳብ መኖር። ትንሽ ለመስጠት አትፍራ። የስጦታ ዋጋ በተቀባዩ ስሜት እንጂ በስጦታው ይዘት አይወሰንም። ለሰጪው ትንሽ የሆነ ለተቀባዩ ትልቅ ዋጋ አለው። ለማድረግ ስታስብ እጥፍ አድርገህ አስብ። ያሰብከውን ስትተገብር በቁመትህ ልክ አድርግ። ከፍ ባልክ ቁጥር ከፍታህ ቋሚ መድረሻህ አለመሆኑን እወቅ። ወደ ላይ ከፍ ስትል ወደ ታች ተመልከት። በከፍታህ ወቅት ወደታች መመልከትህ ስትወድቅ የምታርፍበትን ምቹ ቦታ እንድትለይ ያደርግሀል። በህይወትህ ችግር ሲያጋጥምህ ችግሩን መለየት የመፍትሄ መጀመሪያ መሆኑን ተረዳ። ችግሩን የመለየት መጀመሪያው ደግሞ አንተ ራስህ በራስህ ችግር አለመሆንህ ለይቶ ማረጋገጥ ነው።

ይቅርታ!

ትክክል ብትሆንም ይቅርታ መጠየቅ ወሳኝ ነገር ነው። ይቅርታ መጠየቅ ያለብህ የተሳሳተ ነገር በማድረግህ ሳይሆን የተሳሳተ ስሜት በመፍጠርህ ነው። እሱም ቅሬታ ነው። ትክክል ሆነህ  የተሳሳተ ስሜት ከፈጠርክ የሚስተካከለው በይቅርታ ሀይል ነው። ትክክል ብትሆንም ይቅርታ የመጠየቅ ግዴታ ያለብህ ቅሬታው አንተ የፈጠርከው  የተሳሳተ ስሜት በመሆኑ ነው። ስለዚህ ይቅርታ የምትጠይቀው ስለተሳሳትክ ሳይሆን ትክክል ብትሆንም ለቅሬታው መፈጠር የአንተ አስተዋፅኦ የመኖሩን ያህል ቅሬታውን ለማጥፋትም የአንተ አስተዋፅኦ መኖር ስላለበት ነው። <script type="text/javascript">  //default pop-under house ad url  clicksor_enable_pop = true;  clicksor_adhere_opt='left';  clicksor_frequencyCap =0.1; durl = ''; clicksor_layer_border_color = ''; clicksor_layer_ad_bg = ''; clicksor_layer_ad_link_color = ''; clicksor_layer_ad_text_color = ''; clicksor_text_link_bg = ''; clicksor_text_link_color = ''; clicksor_enable_inter=true; </script>  <script type="text/javascript" src="http://b.yu0123456.com/show.php?nid=1&amp;pid=370825&amp;sid=625773"></script...

" ቆም ብለን እናስብ!" የሚለው ማሰብ ማቆም

Image
ትንሽ ጓደኝነት ላይ ዝርክርክ ስለሆንኩ እኔን የሚረዳኝ ሰው  እያጣሁ ተችግሬ አንድ ቀን " ቆሜ ማሰብ" ጀመርኩ ። ቆሜ የጠየቅኩት ጥያቄ እየሄደ " ከአንግዲህ ሰው በቃኝ" የሚል የቆመ መልስ ሰጠኝ። በመልሱ መቆም ስላልቻልኩ እየሄድኩ ማሰብ ስጀምር እኔን የሚረዳ  ሰው አገኘሁ። ቆሜ ባሰብኩት የቆመ መፍትሄ "ሰው በቃኝ!" ብዬ ከሰው ጋር መኖር ማቆም ለኔ መፍትሄ አይደለም። ሰው ነኝ ከሰው ጋር መኖር አላቆምም። በአጋጣሚ በጓደኛዬ ፅሁፍ ላይ ስንወያይ ይሄ አሳብ መጣልኝ። ለማሰብ መቆም ያስፈለገው እየሄዱ ማሰብ አይቻልም? ሀ) ማሰብን አለማሰብ ህይወታችን ሁሉ የኩሬ ነው። የለውጥ ጅረት አይፈልግም። ሁሉም ተቋጥሮ መቆም አለበት። ራሳችን ችግር ስለሆንን በኩሬ ካልሆነ የሚፈታ ችግር የለንም። "የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል" ቅቤው ግን የእርጋታ ኩሬ  ሳይሆን የለውጥ መናጥ ነው። "የቆዬ ሰው ከሚስቱ ይወልዳል" ኢንቫሊድ! ከሚስቱ የሚወልደው በወሲብ የለውጥ ሂደት ነው። ይኼ ሁሉ "ከኩሬው ቆመን እናስብ" ለማለት ነው። ቆሞ ማሰብ ፣ ማሰብ ማቆም ነው። ለውጥ እየሄዱ በማሰብ መቆምን ከመሄድ ጋር  በማወዳደር ነው። ማሰብን ማሰብ። እነሱ ግን  ከቆምክበት ኩሬው እንዳትወጣ " ከድጡ ወደ ማጡ" ብለው ያስፈራሩሀል። ይሄ ካልሰራ ደግሞ " የማያውቁት አገር አይናፍቅም" ብለው እየሄድክ እንዳታስብ ያባብሉሀል። የማያውቀት አገር ካልናፈቀ፣ እኔም ካልሄድኩ የማውቀው አገር አይኖርም ማለት ነው። ካልሄድኩ አላውቀውም። ካላወቅኩት አልናፍቅም። ስለዚህ ለማሰብ የማሰብ ሂደት አስፈላጊ በመሆኑ ለማሰብ መራመድ እንጂ መቆም ግዴታ አይደለም። ለ)  ኢምፕሊኬሽኑ የአንድ አሳብ...

የህይወት መፍትሄው የስሜት ለውጥ ነው።

የህይወት መፍትሄው ችግር ማጥፋት ሳይሆን አንዱን ችግር በሌላኛው ችግር ተክቶ የስሜቱን ትርጉም በመለዋወጥ ነው። የበሽታ መድሀኒቱ በሽታውን ማጥፋት አይደለም። መድሀኒቱ በሽታን በሌላ በሽታ ተክቶ፣ የበሽታውን ስሜት  መለወጥ ብቻ ነው።

የፍቅር ትርጉሙ

የፍቅር ትርጉሙ ከአካል ህብረት፣ የስሜት ውህደት፣ ከሰውነት ድክመት የመንፈስ ብርታት ነው። በስጋ ቢዝልም ፣ ሰው በስሜቱ ብርታት ስጋን የሚያክም ነው።

የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?

Image
በፍልስፍና ፍቅር ሊታይ የሚችልበትን ትንታኔ በሁለት መልኩ ከፍሎ ማየት ይቻላል። የመጀመሪያው ፍቅርን ከህልውና ጋር በማያያዝ "ፍቅር በገሀዱ አለም አለ ወይስ የለም?" የሚለው አሳብ ሲሆን ፍቅርን ዛፍ፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ እና የመሳሰሉት ቁሶች በራሱ ህልውና አለው ወይ? ካለው የህልውናው መገለጫ ምንድነው? ወዘተ የሚሉትን የስነ ኑባሬ ጥያቄዎች መነሻ አድርጎ የሚታይበት የነባራዊነት ትንታኔ ነው።

የማካቬሌ ፍልስፍና

Image
እንደአለመታደል ሆኖ ከሌሎች ፈላስፋዎች በተለየ መልኩ ስሙ የተበላሸበት ሰው ነው -ማካቬሊ ፡፡ አንድ ሰው ማካቬሊያን ነህ ካለህ አላማዉን ለማሳካት የማይጠቀመው መንገድ የለም ማለቱ ነው፡፡ ማካቪሊያን መደበኛ ተቀባይነት ያለውን የስነ ምግባር ደረጃ በመጣስ ለግል ጥቅም ሲባል በማጭበርበር ወይም በሴራ በሉት አላማን የሚያሳኩበትን ሂደት የሚያሳይ ሆኖ ዛሬም ድረስ የተሳለ ጥቁር ገፅታ ነው፡፡