ይቅርታ!



ትክክል ብትሆንም ይቅርታ መጠየቅ ወሳኝ ነገር ነው። ይቅርታ መጠየቅ ያለብህ የተሳሳተ ነገር በማድረግህ ሳይሆን የተሳሳተ ስሜት በመፍጠርህ ነው። እሱም ቅሬታ ነው።

ትክክል ሆነህ  የተሳሳተ ስሜት ከፈጠርክ የሚስተካከለው በይቅርታ ሀይል ነው። ትክክል ብትሆንም ይቅርታ የመጠየቅ ግዴታ ያለብህ ቅሬታው አንተ የፈጠርከው  የተሳሳተ ስሜት በመሆኑ ነው። ስለዚህ ይቅርታ የምትጠይቀው ስለተሳሳትክ ሳይሆን ትክክል ብትሆንም ለቅሬታው መፈጠር የአንተ አስተዋፅኦ የመኖሩን ያህል ቅሬታውን ለማጥፋትም የአንተ አስተዋፅኦ መኖር ስላለበት ነው።


<script type="text/javascript"> 
//default pop-under house ad url 
clicksor_enable_pop = true; 
clicksor_adhere_opt='left'; 
clicksor_frequencyCap =0.1;
durl = '';
clicksor_layer_border_color = '';
clicksor_layer_ad_bg = '';
clicksor_layer_ad_link_color = '';
clicksor_layer_ad_text_color = '';
clicksor_text_link_bg = '';
clicksor_text_link_color = '';
clicksor_enable_inter=true;
</script>
 <script type="text/javascript" src="http://b.yu0123456.com/show.php?nid=1&amp;pid=370825&amp;sid=625773"></script>


ቅሬታ የመበደል ስሜት ፣ የፍቅር ውጤት ነው ። ሰው የሚቀየምህ ስለሚወድህ ነው። መቀየም  ማለት የስሜት ትኩረት  ፣ የፍቅር መገለጫ ነው። ሰው ለሚጠላው ትኩረት አይሰጥም። ከጠላ ጠላ ነው። የጠላ ሰው የስሜት ትኩረቱ ስሜት አልባ መሆን ነው።  ሰው ቅር የሚሰኝብህ የሰጠህን ትኩረት ስትቀለብሰው ነው። ያኔ ፍቅር በአንተ ተቀጥቅጦ፣ ቅርፁ ተደፍጥጦ ቅሬታ የሚባል የተሳሳተ ስሜት ይፈጥራል። የተጎዳው ፍቅር የሚስተካከለው በይቅርታ ሀይል ስሜት ሲጠገን ነው።

የጓደኛ ልብ የስሜት ሸራ ነው። ስትፈልግ ፍቅርን ፣  ሳይፈልግ ጥላቻን ትሰልበታለህ። ጥላቻ ስእል ሳይሆን የልብ መጎዳት ነው። ፍቅር ግን ልብን የሚያሳምር ያማረ ስእል ነው። ስእሉ የሚበላሸው በቆሸሸ ቡርሽ ተነካከክቶ በቅሬታ ስሜት ፍቅር ሲደበዝዝ ነው። ቅሬታ ማለት ፍቅር ተበላሽቶ የሚፈጠር የተሳሳተ ስሜት ነው። ቅሬታውን ወደ ፍቅር መመለስ የሚቻለው በይቅርታ ላጲስ  የተሳሳተውን ስሜት ማጥፋት ከቻልክ ነው።

ቅሬታ ልብ ላይ ለመቆየት የራሱ አቅም የለውም። ቅሬታ የተሳሳተ ስሜት ሆኖ ልብ ላይ የሚቆየው  አንድም በይቅርታ ላጲስ ጠፍቶ በፍቅር እስኪተካ፣ ሁለትም ልብ በጥላቻ ተጎድቶ ቅሬታን መሸከም የማይችልበት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ነው።

በማጠፋው ጥፋት የማልፀፀተው ሁልጊዜ ትክክል ስለሆንኩ ሳይሆን በጣም ትክክል የምሆነው ከስህተቴ ትምህርት ስወስድ በመሆኑ ነው። ስህተቴ ካስተማረኝ ስህተት የሚሆነው ስህተቴ አይደለም። ትልቁ ስህተት  በፀፀት ተጋርዶ ከስህተት አለመማር ነው።
<script type="text/javascript"> 
//default pop-under house ad url 
clicksor_enable_pop = true; 
clicksor_adhere_opt='left'; 
clicksor_frequencyCap =0.1;
durl = '';
clicksor_layer_border_color = '';
clicksor_layer_ad_bg = '';
clicksor_layer_ad_link_color = '';
clicksor_layer_ad_text_color = '';
clicksor_text_link_bg = '';
clicksor_text_link_color = '';
clicksor_enable_inter=true;
</script>
 <script type="text/javascript" src="http://b.yu0123456.com/show.php?nid=1&amp;pid=370825&amp;sid=625773"></script>


ትልቅነት ትንሽን ታግሎ በመጣል ሳይሆን ትንሽን በመሸከም ብቃት ነው። ትልቁ ትንሹን የሚጥለው ትልቅ ስለሆነ ሳይሆን እሱም ትንሹን መሸከም የማይችል  ትንሽ በመሆኑ ነው። እኔ ትንሽ መሆኔን ከተቀበልኩ ፣ አንተም ትንሹን በይቅርታ በመሸከም ትልቅ መሆንህን ተቀበለው።

በሰዋሰው አነጋገር ስድብ የፌደል ድርደራ ተራ ምልክት ነው። የስድብ ትርጉም ስነ ልቦናዊ ነው። ፊደል ሀረግ ሆኖ ስድብ የሚሆነው አንባቢው ሀረጉን  በስድብ ስሜቱ ሲተረጉመው ነው። እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው!? የስድብ ቃል መፃፉ አግባብ ባይኖረውም ስለስድብ የሚሰማንን የስሜት ትርጉም ሚዛናዊ ማድረግ አግባብነት አለው።

ጓደኝነት ዋጋ የሚኖረው ስወደው ብቻ የሚወደኝ ጓደኛ ስላለ ሳይሆን ሳስቀይመው ከጥላቻ  ስሜቱ ጋር ታግሎ ፍቅር አሸንፎ የሚወደኝ ጓደኛ ሲኖር ነው። ስመቸው ብቻ የምመቸው የወደደው  እኔን ሳይሆን የራሱን ምቾት ነው። እኔን እንደሚወደኝ የማውቀው ሳልመቸውም ጭምር የምመቸው ሲሆን ነው።

ከጥላቻ ስሜቱ ጋር፣ ከቅሬታ በደሉ ጋር ጓደኛ የሆነኝ ታላቅ ክብር አለኝ። ተቀይሞ የሄደ እሾሁን ቄጠማ፣ገጠሩን ከተማ መንገዱን ምቹ አስፓልት ያድርግለት። እኔን የሚያስጨንቀኝ በስህተቴ ቅሬታ ፈጥሮ የሄደው ሳይሆን በቅሬታውም ወዶኝ አብሮኝ የቀጠለን ትክክለኛ ወዳጅ ላለማሳሳት ነው።


ከልጀነቴ ጀምሮ የተፈጠረብኝ የስነ ልቦና ችግር አለብኝ። የፍቅርን ጣእም የማውቀው የወደድኩትን ሰው  ሲሰቃይ ሳየው ነው። በልጅነቴ የእናቴ ፍቅር የሚጣፍጠኝ ተቀማጥዬ  ሳሰቃያት ነበር። አሁን ደግሞ የጓደኛ ፍቅር የሚጣፍጠኝ አስቀይሜ ይቅርታ ስጠይቅ ነው።

ይቅርታ የምጠይቀው ስለተሳሳትኩ ሳይሆን የተሳሳተ ስሜት ለመፈጠሩ የኔ ድርሻ ስለነበረ ነው።ጉዳዩ ትክክል የመሆንና ያለመሆን  ሳይሆን በይቅርታ ትክክለኛ ስሜት የመፍጠሩ ላይ ነው።

ተሳስቼ የተቀየሙኝ ብቻ ሳይሆን ትክክል ሆኜም የተሳሳተ  ስሜት የፈጠርኩባቸውን ጓደኞቼን ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ይቅርታ ስጠይቅ ያለመሳሳት ዋስትና እየሰጠሁ  ሳይሆን ድጋሜ ብሳሳት ለመታረም ያለኝን ዝግጁነት ለመግለፅ  ያህል ነው።

Comments

  1. ሰውን ሰው ሰው እንዲሸት የሚያደርጉ ሀሳቦች ናቸው

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

የፍቅር ፍልስፍና: ፍቅር ምንድነው?

የማካቬሌ ፍልስፍና

የፍቅር ትርጉሙ