" ቆም ብለን እናስብ!" የሚለው ማሰብ ማቆም
ትንሽ ጓደኝነት ላይ ዝርክርክ ስለሆንኩ እኔን የሚረዳኝ ሰው እያጣሁ ተችግሬ አንድ ቀን " ቆሜ ማሰብ" ጀመርኩ ። ቆሜ የጠየቅኩት ጥያቄ እየሄደ " ከአንግዲህ ሰው በቃኝ" የሚል የቆመ መልስ ሰጠኝ። በመልሱ መቆም ስላልቻልኩ እየሄድኩ ማሰብ ስጀምር እኔን የሚረዳ ሰው አገኘሁ። ቆሜ ባሰብኩት የቆመ መፍትሄ "ሰው በቃኝ!" ብዬ ከሰው ጋር መኖር ማቆም ለኔ መፍትሄ አይደለም። ሰው ነኝ ከሰው ጋር መኖር አላቆምም። በአጋጣሚ በጓደኛዬ ፅሁፍ ላይ ስንወያይ ይሄ አሳብ መጣልኝ። ለማሰብ መቆም ያስፈለገው እየሄዱ ማሰብ አይቻልም? ሀ) ማሰብን አለማሰብ ህይወታችን ሁሉ የኩሬ ነው። የለውጥ ጅረት አይፈልግም። ሁሉም ተቋጥሮ መቆም አለበት። ራሳችን ችግር ስለሆንን በኩሬ ካልሆነ የሚፈታ ችግር የለንም። "የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል" ቅቤው ግን የእርጋታ ኩሬ ሳይሆን የለውጥ መናጥ ነው። "የቆዬ ሰው ከሚስቱ ይወልዳል" ኢንቫሊድ! ከሚስቱ የሚወልደው በወሲብ የለውጥ ሂደት ነው። ይኼ ሁሉ "ከኩሬው ቆመን እናስብ" ለማለት ነው። ቆሞ ማሰብ ፣ ማሰብ ማቆም ነው። ለውጥ እየሄዱ በማሰብ መቆምን ከመሄድ ጋር በማወዳደር ነው። ማሰብን ማሰብ። እነሱ ግን ከቆምክበት ኩሬው እንዳትወጣ " ከድጡ ወደ ማጡ" ብለው ያስፈራሩሀል። ይሄ ካልሰራ ደግሞ " የማያውቁት አገር አይናፍቅም" ብለው እየሄድክ እንዳታስብ ያባብሉሀል። የማያውቀት አገር ካልናፈቀ፣ እኔም ካልሄድኩ የማውቀው አገር አይኖርም ማለት ነው። ካልሄድኩ አላውቀውም። ካላወቅኩት አልናፍቅም። ስለዚህ ለማሰብ የማሰብ ሂደት አስፈላጊ በመሆኑ ለማሰብ መራመድ እንጂ መቆም ግዴታ አይደለም። ለ) ኢምፕሊኬሽኑ የአንድ አሳብ...