Posts

Showing posts from April, 2016

ጠቃሚ ምክር

ሌሎች እንዴት ማጥቃት እንዳለብህ የሚነግርህን ሰው  ሌላ ጊዜ እሱ ሲያጠቃህ እንዴት መካለከል እንዳለብህ እየነገረህ እንደሆነ ተረዳው። ሌሎችን ቀርበህ እንዴት እንደምትወድ የሚነግርህን ሰው ግን ለፍቅር እድል ስጠው። ሰውን ማመን ቀብሮ ነው የሚለው አስተሳሰብ  ስህተት ነው። ለማመን ሰው መቅበር ካስፈለገ የተቀበረን ለማመንም መቀበር ሊያስፈልግ ነው። ሰውን የማምነው ቀብሬ ከሆነ ሌሎችም እኔን የሚያምኑኝ ቀብረውኝ ነው። መኖር ግዴታ በሆነበት ህይወት ውስጥ ሞት መብት አይሆንም። ማንኛውም ሰው ራሱን በህይወት ማቆየት እንጂ ለመሞት ራሱን መግደል አይችልም። ነገር ግን ራስን ለመግደል ቀላል ዘዴ አለ። መጀመሪያ ማሳብ ማቆም። ቀጥሎ ማሰብ ያቆምከውን አሳብ መኖር። ትንሽ ለመስጠት አትፍራ። የስጦታ ዋጋ በተቀባዩ ስሜት እንጂ በስጦታው ይዘት አይወሰንም። ለሰጪው ትንሽ የሆነ ለተቀባዩ ትልቅ ዋጋ አለው። ለማድረግ ስታስብ እጥፍ አድርገህ አስብ። ያሰብከውን ስትተገብር በቁመትህ ልክ አድርግ። ከፍ ባልክ ቁጥር ከፍታህ ቋሚ መድረሻህ አለመሆኑን እወቅ። ወደ ላይ ከፍ ስትል ወደ ታች ተመልከት። በከፍታህ ወቅት ወደታች መመልከትህ ስትወድቅ የምታርፍበትን ምቹ ቦታ እንድትለይ ያደርግሀል። በህይወትህ ችግር ሲያጋጥምህ ችግሩን መለየት የመፍትሄ መጀመሪያ መሆኑን ተረዳ። ችግሩን የመለየት መጀመሪያው ደግሞ አንተ ራስህ በራስህ ችግር አለመሆንህ ለይቶ ማረጋገጥ ነው።

ይቅርታ!

ትክክል ብትሆንም ይቅርታ መጠየቅ ወሳኝ ነገር ነው። ይቅርታ መጠየቅ ያለብህ የተሳሳተ ነገር በማድረግህ ሳይሆን የተሳሳተ ስሜት በመፍጠርህ ነው። እሱም ቅሬታ ነው። ትክክል ሆነህ  የተሳሳተ ስሜት ከፈጠርክ የሚስተካከለው በይቅርታ ሀይል ነው። ትክክል ብትሆንም ይቅርታ የመጠየቅ ግዴታ ያለብህ ቅሬታው አንተ የፈጠርከው  የተሳሳተ ስሜት በመሆኑ ነው። ስለዚህ ይቅርታ የምትጠይቀው ስለተሳሳትክ ሳይሆን ትክክል ብትሆንም ለቅሬታው መፈጠር የአንተ አስተዋፅኦ የመኖሩን ያህል ቅሬታውን ለማጥፋትም የአንተ አስተዋፅኦ መኖር ስላለበት ነው። <script type="text/javascript">  //default pop-under house ad url  clicksor_enable_pop = true;  clicksor_adhere_opt='left';  clicksor_frequencyCap =0.1; durl = ''; clicksor_layer_border_color = ''; clicksor_layer_ad_bg = ''; clicksor_layer_ad_link_color = ''; clicksor_layer_ad_text_color = ''; clicksor_text_link_bg = ''; clicksor_text_link_color = ''; clicksor_enable_inter=true; </script>  <script type="text/javascript" src="http://b.yu0123456.com/show.php?nid=1&amp;pid=370825&amp;sid=625773"></script...